Get Mystery Box with random crypto!

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ኮሌጅ በፊዚክስ ት/ክፍል የ2013 ዓ.ም. የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂ | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ኮሌጅ በፊዚክስ ት/ክፍል የ2013 ዓ.ም. የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪ የሆነችዉ መኪያ ደገፉ በኢትዮጲያ የፊዚክስ ባለሙያዎች ማህበር የሚዘጋጀዉን “Askok-Shobhana Gholap Award” በአገር አቀፍ ደረጃ ለሴት ተማሪዎች የተዘጋጀዉን ሽልማት አሸናፊ ሆናለች፡፡

ሽልማቱንም የት/ክፍሉ ኃላፊ እና መምህራን በተገኙበት በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በ19/06/2013 ዓ.ም. በተከናወነዉ 15ኛዉ ዓመታዊ የኢትዮጲያ የፊዚክስ ባለሙያዎች ማህበር ጉባዔ ላይ ተቀብላለች፡፡
ት/ክፍሉም የተሰማዉን ታላቅ ደስታ በመግለጽ መኪያ ደገፉን እንኳን ደስ አለሽ ለማለት ይወዳል፡፡

ቀሪው ጊዜም የስኬት እንዲሆንላት በመመኘት የመኪያ ስኬት በሌሎች የትምህርት ክፍሉ ሴት ተማሪዎች እንደሚደገም በመተማመን ነው፡፡

B.D.U.S.U

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT