Get Mystery Box with random crypto!

ልጆችን ለማነፅ ቀላል ከሆኑ መንገዶች፦ •┈┈••••○○❁ ❁○○••••┈┈• ➏ ልጃቸው ፊት | 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺

ልጆችን ለማነፅ ቀላል ከሆኑ መንገዶች፦
•┈┈••••○○❁ ❁○○••••┈┈•

➏ ልጃቸው ፊት የሚስማሙ፣ የሚግባቡ፣  የማይጨቃጨቁና የማይጯጯሁ አባትና እናት ልጆቻቸውን ቤታቸውን እንዲወዱ፣ እርስ በእርስ የሚግባቡ፣ የሚዋደዱና የሚቀራረቡ እንዲሆኑ ያደርጓቸዋል።

➐ አባት ዝምድና የሚቀጥል ለነሱም በጎ የሚውልላቸውና የሚወዳቸው ከሆነ ልጆቹ ዝምድናን መቀጠልንና ለነሱ በጎ መዋልን ይማራሉ።

➑  አንዳንድ ነጥቦች ላይ የልጆቹንና የባለቤቱን ሃሳብ የሚቀበል ከእነርሱ ጋር የሚወያይና ራዕያቸውን የሚያከብር አባት ልጆቹን መመካከርንና አዎንታዊ (ሀሳብ ተቀባይ)
መሆንን ያስተምራቸዋል።

➒ ከልጆቹ ጋር እውነተኛ የሆነ አባት እውነትን ያስተምራቸዋል። እንዲሁም የገባውን ቃል የሚፈፅምላቸው ከሆነ ለሰዎች የገቡትን ቃል መሙላትን ያስተምራቸዋል።

➓ንጽህናንና ስርዓትን የሚጠብቁ በፕሮግራም የሚመሩ አባትና እናት ልጆቻቸውን ስርዓት ያለው ኑሮ እንዲኖሩ ያደርጓቸዋል።

➬ማጠቃለያው በልጆች አስተዳደግ ላይ ውጤታማ ለመሆን፦

እናንተ መስራት እየቻላችሁ የማትሰሩትን ነገር ልጃችሁ እንዲሰራ አትፈልጉ።

አንድን ክልክል የሆነን ነገር እናንተ ፊታቸው የምትሰሩት ሆኖ ሳለ አትከልክሏቸው።


መልካም አርአያ በመሆን ልጅን ማሳደግ ቀላሉ የተርቢያ መንገድ ነው።
•┈┈••••○○❁ ❁○○••••┈┈•

አላህ ይወፍቀን።

#ተርቢያ
@nesiha_ouserya