🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

በመጀመሪያው የግንኙነት ለሊት ምን ማድረግ ይገባል ۩••۩┈┈┈•⊰۩ ۩⊱•┈┈┈۩••۩ ጥያ | 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺

በመጀመሪያው የግንኙነት ለሊት ምን ማድረግ ይገባል
۩••۩┈┈┈•⊰۩ ۩⊱•┈┈┈۩••۩
ጥያቄ፡
በጋብቻ ቀን ለሊት ለባልና ሚስት ሱናው ምንድነው? ከነብዩ የተገኙ ዱዓዎችንና ስራዎችን እንድትጠቅሱልን እንፈልጋለን፡

መልስ፡
●ባል ከሚስት ጋር በሚገናኝበት ለሊት ትኩረት ሊሰጣቸው ከሚገቡ ነገሮች ውስጥ፦

►ለሷ ክንፉን ዝቅ አድርጎ(ተረጋግቶና) ጭርታን በሚያስወግድ መልኩ ወደሷ መግባት አለበት። ምክንያቱም በዚህ ሰአት ጭንቀትና ፍርሀት እሷ ዘንድ ይኖራልና።

►ሯሷን ይዞ የሚታወቀውን ዱዓ ያድርግ
"አላህ ሆይ! ከኸይር ነገሯና በእሱ ላይ እሷን የፈጠርክበትን ኸይር እጠይቅሀለሁ፡ ከሸሯና በእሱ ላይ እሷን ከፈጠርክበት ሸር በአንተ እጠበቃለሁ"፡ ይህንን በግልጽ (ድምጹን ከፍ አርጎ) ይበል፡ ምናልባት ሰግታ "ምንድነው? በኔ ላይ ሸር አለ?" ትላለች ብሎ ካልፈራ በስተቀር፡ ይህን ከፈራ እጁን ራሷ ላይ አስቀምጦና ድምጹን ዝቅ አርጎ መቅራት በቂ ነው።

►ሁለተኛው የአላህ መልእክተኛ -ﷺ- አንድ ሰው ከባለቤቱ ጋር ግንኙነት ሲያደርግ እንዲል ያነሳሱበትን ዚክር ይበል

▹<<አንዳቹህ ወደሚስቱ ሲመጣ "በአላህ ስም! አላህ ሆይ እኛን ከሸይጧን ጠብቀን፡ የምትሰጠንንም ከሸይጧን ጠብቅ" ካለ በመካከላቸውም ልጅ ከተቀደረ ሸይጧን መቼም አይጎዳውም>>

▹ይሄ ልጆችን ከማስተካከያ ሰበቦች ነው። ቀለል ያለም ሰበብ ነው።

●ልክ እንደዚሁ መገንዘብና ማወቁ ከሚያስፈልግ ነገሮች… ግንኙነት እስካረጉ ድረስ የዘር ፈሳሽ ባይፈስም በሁለቱም በኩል ገላን መታጠብ ግድ ይላል።ከፊሎች በተቃራኒው መታጠብ ግድ የሚለው የዘር ፈሳሽ ሲፈስ ነው ብለው ያስባሉ ይሄ እሳቤ ስህተት ነው።ምክንያቱም ነብዩ -ﷺ- <<በአራት ቅርንጫፎቿ መሀል ከተቀመጠና ግንኙነት ከፈፀመ የዘር ፈሳሽ ባይፈስም ትጥበት ግድ ሆኗል>>ብለዋልና።

►በዚህም ከሁለት በአንዱ ትጥበት ግድ ይላል፡ ወይ የዘር ፈሳሽ በመውጣት ወይም በግንኙነት። የዘር ፈሳሽ የወጣው በመሳሳም ቢሆን በመተቃቀፍም ቢሆን ወይ በስሜት በማየትም ሆነ በመነጋገር በየትኛውም ቢሆን መታጠብ ግድ ነው።ግንኙነት ተደርጎም የዘር ፈሳሽ ባይወጣም መታጠብ እንዲሁ ግድ ነው።

►ብዙ ሰዎች ግንኙነት ፈፅመው በወቅቱም የዘር ፈሳሽ ካልወጣ እንደማይታጠቡና በዚህም ብዙ ወራት እንዳለፉ (ምን ማድረግ እንዳለባቸው) ይጠይቁናል። የዚህ ምክንያቱ የሚያገባ ሰው በጋብቻ ወቅት ምን ማድረግ እንደሚገባና ምን ግዴታ እንደሆነ አይጠይቅም። ብዙዎቹም ሰዎች እንደዚህ አይነት ትምህርቶችን በወጣቶች መካከል አያሰራጩም።
۩••۩┈┈┈•⊰۩ ۩⊱•┈┈┈۩••۩
لِلشَّــيْخ العَلّامـَـة/ مُحَـمَّد بـنُ صَـالِح العُثَـيْمِين -رَحِــمَهُ الله-

#ትዳር
@nesiha_ouserya