🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ልጆች ከአላህ የሆኑ ፀጋና ስጦታዎች ናቸው። አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ ይላል፦ {لِّ | 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺

ልጆች ከአላህ የሆኑ ፀጋና ስጦታዎች ናቸው።

አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ ይላል፦

{لِّلَّهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ يَهَبُ لِمَن يَشَاءُ إِنَاثًا وَيَهَبُ لِمَن يَشَاءُ الذُّكُورَ
أَوْ يُزَوِّجُهُمْ ذُكْرَانًا وَإِنَاثًا ۖ وَيَجْعَلُ مَن يَشَاءُ عَقِيمًا ۚ إِنَّهُ عَلِيمٌ قَدِيرٌ } [الشورى : 49-50]

የሰማያትና የምድር ንግሥና የአላህ ነው፡፡ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ ለሚሻው ሰው ሴቶችን (ልጆች) ይሰጣል፡፡ ለሚሻውም ሰው ወንዶችን ይሰጣል፡፡
ወይም ወንዶችና ሴቶች አድርጎ ያጠናዳቸዋል፡፡ የሚሻውንም ሰው መካን ያደርገዋል፡፡ እርሱ ዐዋቂ ቻይ ነውና፡፡

ሱረቱ ሹራ 49-50

አላህ በዚህ አንቀፅ ላይ ስለ ልጆች ሲገልፅ ሴቶችን ከወንዶች ያስቀደመበትን ምክንያት ኢብን ዐጢያ በተፍሲራቸው ሲያብራሩ

➬ይህ የሴቶችን ክብርና እነሱን መጠበቅና ለነሱ በጎ መዋልን የሚያሳስብ ነው ብለዋል።

ልጅ መሰጠትን በተመለከተ ሰዎች ለ4 ተከፍለዋል።

1. ሴት ልጆች ብቻ የተሰጣቸው
እንደ ነብዩላህ ሉጥ

2. ወንድ ልጆች ብቻ የተሰጣቸው
እንደ ነብዩላህ ኢብራሒም

3. ሴትና ወንድ የተሰጣቸው እንደ ነብዩ ሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም

4. ልጅን ያልተሰጡ
እንደ ነብዩላህ የህያ

ያ አላህ! ልጆቻችንን በመልካም በማነፅ ተግባራዊ ምስጋና የምናደርስ ባሮች አድርገን።

#ተርቢያ
@nesiha_ouserya