🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

#ወሳኝ ቁጥር አንድ ውድና የተከበራችሁ ወላጆች ልጆችን በኢስላማዊ ተርቢያ በማነፅ ሂደት ውስጥ | 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺

#ወሳኝ ቁጥር አንድ

ውድና የተከበራችሁ ወላጆች ልጆችን በኢስላማዊ ተርቢያ በማነፅ ሂደት ውስጥ ወሳኝ የሆነውን ነጥብ እንጠቁማቹ ።
•• ● ••

ሰዒድ ቢን ጁበይር (رحمه الله) የተባሉ ታብእይ
"እኔ ለልጄ ስል ሰላትን እጨምራለሁ " ይሉ ነበር።
••●••
➬ይህንን ንግግር ሸይኽ አብዱረዛቅ አልበድር ሲያብራሩት እንዲህ ይላሉ፦

በዘመናችን ለልጆች ከሚያስፈልጋቸው ነገር ዋናው የዚህ አይነት እውነተኛ የሆነ የወላጆች እዝነት ነው።ይህም ሰላትን በማርዘም ልጆችን ቀልባቸውን እንዲያበጅ፣ነፍሳቸውን እንዲያጠራ፣ከፈተና እንዲጠብቃቸው፣በዲን ላይ እንዲያፀናቸው፣አላህን በመማፀንና በዱዓ ችክ በማለት(በመዘውተር) ነው።

በተለይ ከዚህ ወጣቶችን እየጠለፈ ወደ ጥልቅ ስፍራ ከሚከት የፈተና አውሎ ነፋስና ግጭቶች አላህ በቸርነቱ ልጆቻችንን ይጠብቅልን ፣ ይምራቸው እንዲሁም ያስተካክላቸው ዘንድ አላህን ዘወትር ልንለምነው ይገባል፡፡
••●••
አላህ ያግራልን።

#ተርቢያ
@nesiha_ouserya