🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የመኝታ ሀቅ(3) ۩••۩┈┈┈•⊰۩ ۩⊱•┈┈┈۩••۩ قال رسول ك تصوم | 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺

የመኝታ ሀቅ(3)

۩••۩┈┈┈•⊰۩ ۩⊱•┈┈┈۩••۩

قال رسول ك تصوم النهار وتقوم الليل قلت بلى يا رسول الله قال فلا تفعل صم وأفطر وقم ونم فإن لجسدك عليك حقا وإن لعينك عليك حقا وإن لزوجك عليك حقا
رواه البخاري
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ፦
"አብደላህ ሆይ! አንተ ቀን እንደምትጾም ለሊት እንደምትሰግድ አልተነገረኝምን?አዎ የአላህ መልዕክተኛ አልኩ።እሳቸውም ይህን አታድርግ።ፁም አፍጥር ስገድ ተኛ።አካልህ ባንተ ላይ ሀቅ አለው፣ዐይንህም ባንተ ላይ ሀቅ አለው፣ባለቤትህም ባንተ ላይ ሀቅ አላት።"
ቡኻሪ ዘግበውታል

በሀዲሱ ሰሃባው ለሊቱን ሙሉ በዒባዳ ማሳለፉ በዚህም የሚስቱን ሀቅ አለመወጣቱ ትክክል እንዳልሆነ ተጠቁሟል።

ባል የሚስቱን ተፈጥሮአዊ የሆነውን የግንኙነት ፍላጎት የሚያሟላው ከሀራምና ከአጸያፊ ነገሮች ርቃ ጥብቅ ትሆን ዘንድ ነው።

"አንድ ወንድ ለኡዝር ቢሆን እንጂ ከባለቤቱ ጋር ግንኙነት መፈፀሙ ግዴታ ነው።"
ይህ የኢማሙ ማሊክ፣የአቢ ሀኒፋ እና የኢማሙ አህመድ አቋም ሲሆን ኢብኑ ተይሚያም ይህን መርጠውታል።

የግዴታው ልክም እሷን በሚያስፈልጋትና ጥብቅነትን ሊያስገኝ በሚችልበት ደረጃ ሊሆን ይገባዋል።

"ባል በራሱ ላይ የዚህ ነገር ድክመት ካለበትና የመኝታ ሀቋን መስጠት ካልቻለ ሚስቱን ጥብቅ ያደርጋት ዘንድ ህክምና ሊያደርግ ይገባል።"
ተፍሲር ቁርጡቢ
۩••۩┈┈┈•⊰۩ ۩⊱•┈┈┈۩••۩
#ትዳር የጋራ ሀቅ
@nesiha_ouserya