قال الله تعالى: ﴿ وَإِنَّ اللَّهَ لَهَادِ الَّذِينَ ءَامَنُوا إِلَى صِرَاطٍ مُسْتَقِيمٍ ﴾ [الحج:٥٤] "አላህም እነዚያን ያመኑትን ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ መሪ ነው።" ሱረቱል ሀጅ 54 ቴክኖሎጂው ባደገበትና በተስፋፋበት ዘመን ልጅን ለማሳደግ የተሻለው ዘዴ በአላህና በመልዕክተኛው ያላቸው እምነት ጠንካራ እና ጥልቅ እንዲሆን ማድረግ ነው። ➬በመጀመሪያ ደረጃ ወደድንም ጠላንም አላህ ከጠበቃቸው በስተቀር ልጆች አላህና መልዕክተኛው የማይወዱትን ነገሮች ሊመለከቱ እንደሚችሉ ወላጆች ማመን አለብን። ➬ሁለተኛ በዚህ ዘመን ልጆችህን በመቆጣጠር የማትወደውን ነገር እንዳይመለከቱ ማድረግ እንደማትችል ማወቅ አለብህ። ዛሬ ላይ ትግሉ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን ከልጅህ ላይ መቀማት ሳይሆን ልጅህ ልብ ላይ እምነትን መዝራት መሆን አለበት። ያ አላህ! ልጆቻችንን ይጠብቅልን።እኛንም መልካም አርአያ አድርገን። #ተርቢያ 1.9K viewsedited 17:27