Get Mystery Box with random crypto!

#ልጆችን በምን እናንፅ? ልጆችዎን ዚክር ያስተምሩ የመልካም ስራ ሚዛንዎን ያክብዱ ሸይኽ ሱ | 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺

#ልጆችን በምን እናንፅ?

ልጆችዎን ዚክር ያስተምሩ
የመልካም ስራ ሚዛንዎን ያክብዱ

ሸይኽ ሱለይማን ሩሀይሊ እንዲህ ይላሉ፦
••●••

ወላጆች ልጆችን በመልካም በማነፅ ሂደት ላይ ከምንዘነጋቸው ነገሮች አንዱ ዚክርን(አላህን ማስታወስን) ማስተማርና በዚህም ላይ ከህጻንነታቸው ጀምሮ (እንዲተገብሩት) ማለማመድ ነው።

ውድ ወላጅ! ልጆቻችንን ሱረቱ ፋቲሃን በማስተማር ላይ ማንም ሊቀድመን አይገባም። ለምን ቢባል ሱረቱል ፋቲሃን ካስተማርናቸው ፋቲሃን በቀሩ ቁጥር አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) አጅራቸውን ለኛም ይፅፍልናል።

ሌሎች ዚክሮችንም ካስተማርናቸውና ያንን ዚክር (ለምሳሌ ሱብሃነላህ ሲሉ) ሞተን ተቀብረን ቢሆን እንኳን አላህ የእነሱን አጅር ይፅፍልናል።በዱንያ ልጆቻችን ዚክር ባደረጉ ቁጥር የኛ አጅር ይቀጥላል።ይህም የሆነው አላህን ማውሳትን በማስተማራችን ነው።

በሚያሳዝን ሁኔታ አብዛኛው ወላጅ ልጆችን አስቂኝ ቀልዶችንና የማይጠቅሙ ዛዛታ..... ነገሮችን በማስተማር ላይ ይገኛል።

ከፊሎችም የማይጎዳቸው ቢሆንም እንኳን የማይጠቅማቸውን ነገር በማስሀፈዝ(በቃላቸው በማስያዝ) ላይ ሲጓጉ በተቃራኒው የሚጠቅማቸው የሆነውን ፋቲሃን ዚክርን የማስሀፈዝና የማለማመድ ተነሳሽነት የላቸውም።
••●••

አንድ ሰው በቀን ቢያንስ 17 ጊዜ ፋቲሃን እንደሚቀራ አስተውለናል?

ለልጆቻችን መልካም ስራዎችን በማስተማር ላይ ቀዳሚ በመሆን ከአጅራቸው ተጋሪ እንሁን።

#ተርቢያ#ዚክር
@nesiha_ouserya