Get Mystery Box with random crypto!

አላሁ ተአላ መልካም ስራ የምንሰራበት የተለያየ አጋጣሚዎችን ለግሶናል። ከዚህም መሀከል የረመዳ | 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺

አላሁ ተአላ መልካም ስራ የምንሰራበት የተለያየ አጋጣሚዎችን ለግሶናል።

ከዚህም መሀከል የረመዳን ወር ልዩ አጋጣሚ ነው።

➤የረመዳን ወር የተከበረ ወር ነው።

➤የረመዳን ወር ቁርአን የወረደበት ወር ነው።

➤የጀነት በሮች የሚከፈቱበት የጀሀነም በሮች የሚዘጉበት ወር ነው።

➤ሸያጢኖችና አስቸጋሪ የሆኑ ጂኖች የሚታሰሩበት ወር ነው።

➤በዚህ ወር "መልካም ስራ ፈላጊ ሆይ ተነስ መጥፎ ስራ ፈላጊ ሆይ ታቀብ!" የሚል ጥሪ ተጣሪ የሚጣራበት ነው።

➤አላሁ ተአላ ብዙ የጀሀነም ሰዎችን ነፃ የሚያወጣበት ወር ነው።

➤በውስጡም ለይለቱል ቀድር (ከ 1000 ወራት የሚበልጥ ለሊት )ያለበት ወር ነው።

አላህ ሆይ! ረመዳንን ወር ደርሰው ከሚጠቀሙበት አድርገን።

@nesiha_ouserya
#መልእክት#ረመዳን