🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

#ልጆችን በምን እናንፅ? #ፆም አንድ ህፃን ልጅ በፆም የ | 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺

#ልጆችን በምን እናንፅ?

#ፆም

አንድ ህፃን ልጅ በፆም የሚታዘዘው መቼ ነው? እስኪያድግ ድረስ ዝም ይባላልን? ወይስ በህፃንነቱ እንዲፆም ይገደዳል?

ወላጅ በልጆቹ ላይ ያለው ሀላፍትና ትልቅ ነው። ይህ ሀላፍትና አላሁ ተአላ በሰው ልጅ ላይ ካስቀመጠው አደራ/አማና/ አንዱ ነው።

አላሁ ተአላ በሚወደው መንገድ የተወጣው ከሆነ እድለኛ ነው አልያ ግን አደራውን ችላ ያለ ከሆነ በዱንያም በአኼራም የከሰረ ይሆናል።

"يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ قُوٓا۟ أَنفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًا وَقُودُهَا ٱلنَّاسُ وَٱلْحِجَارَةُ عَلَيْهَا مَلَٰٓئِكَةٌ غِلَاظٌ شِدَادٌ لَّا يَعْصُونَ ٱللَّهَ مَآ أَمَرَهُمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ" التحريم 6
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከኾነች እሳት ጠብቁ፡፡ በእርሷ ላይ ጨካኞች፣ ኀይለኞች የኾኑ መላእክት አልሉ፡፡ አላህን ያዘዛቸውን ነገር (በመጣስ) አያምጹም፡፡ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ፡፡"
አል ተህሪም 6

"يُوصِيكُمُ ٱللَّهُ فِىٓ أَوْلَٰدِكُمْ " النساء 11
"አላህ በልጆቻችሁ ያዛችኋል፡፡ "አል ኒሳእ 11

ስለዚህ ወላጆች የልጆቻቸው አስተዳደግ ላይ ልዩ ትኩረት ማድረግ አለባቸው። ልጆች ለአቅመ አደም ከመድረሳቸው በፊት አምልኮን/ ኢባዳን/ ሊለማመዱ ይገባል።

ፆም ትእግስት ከሚያስፈልጋቸው የአምልኮ ዘርፍ አንዱ ነው። ስለዚህ ልጆች ካደጉ በኃላ እንዳይከብዳቸው በግዜ ወላጆች ሊያለማምዷቸው ይገባል።

የአላህ መልክተኛ ባልደረባዎች ልጆቻቸውን በህፃንነታቸው ፆምን ያለማምዷቸው ነበር ። የአላህ መልክተኛም አይተው በዝምታ ያልፏቸው ነበር።

የሙአወዝ ልጅ የሆነችው ሩበይእ አላህ ስራዋን ይውደድላትና እንዲህ ትላለች"ህፃን ልጆቻችንን እናፆማቸው ነበር።ወደ መሰጂድም እንሄድ ነበር ። ከጥጥ የተሰራ መጫወቻም እንይዝላቸው ነበር። አንዳቸው ምግብ ፈልጎ ሲያለቅስ ይህን መጫወቻ እንሰጠው ነበር። በዚህ ሁኔታ ፍጡር እስኪደርስ ድረስ እናቆየው ነበር።"
የቡኻሪና የሙስሊም ዘገባ

ለአቅመ አደመ ያልደረሰ ሆኖ ነገር ግን መፆም የሚችል ከሆነ ወላጆች ልጆቻቸውን በፆም ሊያዟቸው ይገባል።ምንም እንኳን ግዴታ ባይሆንባቸውም ይታዘዛሉ። ምክንያቱም የአላህ መልክተኛ ልጁ በቻለ ግዜ በኢባዳ ላይ እንድናዘው ታዘናል።

የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል፦
"مروا أبنائكم بالصلاة لسبع سنين واضربوهم عليها لعشر سنين وفرقوا بينهم في المضاجع"
"ልጆቻችሁ ሰባት አመት የሞላቸው ጊዜ በሰላት እዘዟቸው። በአስር አመታቸው ካልሰገዱ ግረፏቸው። በመኝታ ቦታቸውም ለያዮዋቸው።" የአህመድ ዘገባ

ወላጅ ሆኖ ለልጁ መልካም ነገር የማይመኝ ማንም የለም ሆኖም ግን ልጆች በኢባዳ ላይ ሰነፍ ሆነው እንዲያድጉ ማድረግ የለብንም። ሱብሂ ሰላት ለመስገድ ብርድ ይመታሀል፣ ፆም ለመፆም ይርብሀል በሚል ምክንያት ብቻ ሰነፍ ልናረጋቸው አይገባም።ሁኔታቸውን እያየን ልናጠናክራቸው ይገባል።
T.me/dawudyassin

አላህ ይወፍቀን።

#ተርቢያ#ረመዳን