🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ጾመኛ ማን ነው? ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ~ ጾመኛ ማለት: – አካሎቹን | 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺

ጾመኛ ማን ነው?

ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ~
ጾመኛ ማለት: –
አካሎቹን ከሀጢአት የጸዱ፤
ምላሱን ከአሉባልታ፣ ከውሸት እና ከአጸያፊ ንግግር የጠበቀ፤
ሆዱን ከምግብ ፣ ከመጠጥ እና ብልቱን (በቀን ክፍለ ጊዜ) ከግብረ ስጋ ግንኙነት የጠበቀ ነው።
ጾመኛ :–
ከተናገረ ጾሙን በማይጎዳ
ስራ ከሰራ ጾሙን በማያበላሽበት መልኩ ይሰራል።
ጾመኛ ጠቃሚና ቁምነገር ያለው ንግግር እና ስራ ሲሰራ ምሳሌው ልክ ከሽቶ ተሸካሚ ሰው ጋር ተቀምጦ መልካም ሽታ እንደሚያገኝ ሰው ነው።

ከጾመኛ ጋር የተቀመጠም ሰው መልካም ነገርን እንጂ ሌላ አያገኝም። ከተለያዩ መጥፎ ነገሮች እንደ ቅጥፈት፣ ውሸት፣ ጥመትን እና በደልን ሁሉ ሰላም ይሆናል።

ይህ ነው ትክክለኛና ህጋዊ ጾም ማለት …
ከምግብና መጠጥ ብቻ መታቀብ ጾም አይባልም።
ጾም ማለት አካላትን ከሀጢአት እና ሆድን ከምግብና መጠጥ በመታቀብ መጾም ነወ።

ምግብና መጠጥ ጾምን እንደሚያጠፋ ሁሉ ሀጢአትም የጾምን ምንዳ ያጠፋል፣ ውጤቱን ያበላሻል። በዚህም ምክንያት ልክ ጾም እንዳልጾመ ተደርጎ ይታሰባል።

ምንጭ: –
አልዋቢሉ አሶይብ (31–32)
Te»https://t.me/jemalyassin

#ተርቢያ#ረመዳን