Get Mystery Box with random crypto!

የደስተኛ ትዳር መሰረቶች ➌ በቤት ውስጥ መዋደድ እና መተዛዘን መኖር •┈•⊰✿ ✿⊱ | 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺

የደስተኛ ትዳር መሰረቶች

➌ በቤት ውስጥ መዋደድ እና መተዛዘን መኖር
•┈•⊰✿ ✿⊱•┈•

"...... በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው። ” 
(አርሩም 30፤21)

➪ኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁ ይህን አንቀፅ ሲያብራሩት መወዳ (ዉዴታ) ማለት ባል ሚስቱን መውደዱ ሲሆን ረህማ(እዝነት) ማለት ሚስቱ ክፉ እንዳያገኛት መራራቱ ነው ብለዋል።

እውነተኛ መዋደድ እና መተዛዘን በአላህ ፍራቻ ላይ የተገነባ መሆን አለበት።

በትዳር ውስጥ ውዴታን ከሚያፋፉ ነገሮች አንዱ በመልካም መኗኗር ነው ።

እውነተኛ ውዴታ በእንቅስቃሴያችን በተግባራችን እና በንግግራችን የሚገለፅ ነው ።

ሁሉም ቤቶች በፍቅር እንደማይገነቡ፣ በጥንዶች መካከል መዋደድ በሚቀንስበት (በማይኖርበት)ጊዜ ጥንዶች ወደ ፍቺ ሊጋበዙ እንደማይገባና ትዳሩ በመካከላቸው ባለው እዝነት መቀጠል እንደሚችል ልንረዳ ይገባል።
ውዴታችን ድንበር ያለፈ ከመሆን ጠንቀቅ ማለት ያስፈልጋል። ምክንያቱም በውስጡ የተጠላ የሆነ የልብ መንጠልጠል ስለሚያስከትልና አሰልቺ ስለሚሆን ነው። ከልክ ያለፈ እዝነትም መኖር የለበትም።ባጠቃላይ ሚዛናዊ ልንሆን ይገባናል።
•┈•⊰✿ ✿⊱•┈•
#ትዳር
#nesiha_ouserya