Get Mystery Box with random crypto!

ዙልሒጃ ❾- አረፋ የአረፋ እለት አላህ ዲናችንን ያሟላበትና ፀጋውንም የተሟላ ያደረገበት እለት | 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺

ዙልሒጃ ❾- አረፋ

የአረፋ እለት አላህ ዲናችንን ያሟላበትና ፀጋውንም የተሟላ ያደረገበት እለት ነው።

➣ያቺ እለት አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ
﴿اليَومَ أَكمَلتُ لَكُم دينَكُم وَأَتمَمتُ عَلَيكُم نِعمَتي وَرَضيتُ لَكُمُ الإِسلامَ دينًا﴾
«ዛሬ ሃይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ። ፀጋዬንም በናንተ ላይ የተሟላ አደረግኩኝ። ኢስላምንም በሃይማኖትነት ወደድኩላችሁ።» በማለት የገለፀበት እለት ናት።

የአላህ መልእክተኛ ﷺ

" صيامُ يومِ عرفةَ ، أَحتسبُ على اللهِ أن يُكفِّرَ السنةَ التي قبلَه، والسنةَ التي بعده "

«የዐረፋ እለት ፆም ከዚህ አመት ቀድሞ ያለውንና የቀጣዩን ኣመት እንደሚያስምርልን ከአላህ ኣስባለሁ።» ብለዋል።
ሙስሊም ዘግበውታል

➣ በዚሁ አጋጣሚ ከትልልቅ ወንጀሎቻችን በመፀፀት ወደ ጌታችን እንመለስ (ተውበት እናድርግ)።

የዚህን ቀን ትሩፋት በመሻትም የአረፋ እለትን (ሰኞን) ከቤተሰቦቻችን ጋር በፆም ለማሳለፍ ከወዲሁ እንነይት።

በተጨማሪም የአላህ መልእክተኛ ﷺ
" خيرُ الدعاءِ دعاءُ يومِ عرفَةَ ...."

"ከዱዓኦች በላጩ የዐረፋ እለት ዱዓእ ነው። .."
ብለዋልና በእለቱ ዱዓ ላይ እንጠንክር።

አላህ ይወፍቀን።

http://t.me/nesiha_ouserya