Get Mystery Box with random crypto!

አልሀበሺ እውነታውን ሲያምን!! #መውሊድ መውሊድን የማክበር ሀሳብ ከክርስቲያኖች የገና በአል | 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺

አልሀበሺ እውነታውን ሲያምን!!

#መውሊድ

መውሊድን የማክበር ሀሳብ ከክርስቲያኖች የገና በአል ተኮርጆ የመጣ መሆኑን ላለመቀበል ሀሰን ታጁ እና መሰሎቹ ቢሞግቱም አብደላህ አልሀበሺ በተቃራኒው እውነታውን አምኗል፤

☞ የ ‘ኢዝሀሩል አቂደቲሱኒያህ’ የድምፅ ማብራሪያ ካሴት ቁ.9 የመጀመሪያው ክፍል ላይ የመውሊድን አጀማመር አስመልክቶ፤ መውሊድን ለመጀመሪያ ጊዜ ያከበረው የኢርቢሉ ንጉስ ሙዘፈር እንደሆነ እና አጀማመሩም ክርስቲያኖች የመሲህን ልደት ሲያከብሩ አይቶ ሙሀመድ ﷺ በዚህ አለም ብቅ በማለታቸው አላህን ሊያመሰግን እንደሆነ ያብራራል።

እኛም እውነታዉን በማመኑ እያመሰገነው ተከታዮቹን ነጥቦች እንጠቁማለን፤

1) መውሊድን በዓል አድርጎ ማክበር መልእክተኛው ﷺ ወደዚህ አለም በመምጣታቸው ለአላህ ምስጋና የማቅረቢያና ውዴታንም የመግለጫ መንገድ ከሆነ ከሰሀቦችና ታቢዒዮች ዘመን ጀምሮ የኖሩ ምርጥ የኢስላም ልጆች ሳያውቁት በ630 ዓ.ሒ የሞተው ንጉስ ተገለጠለትን?

2) በላጭ ትውልዶች የተባሉት ቀደምቶቹ ሰለፎች ይህንን መውሊድ ያላከበሩት፤ ክርስቲያኖችና አህባሾች የደረሱበትን መውሊድ አላህን የማመስገኛ መንገድ የመሆኑን እውነታ ማወቅ ተስኗቸው ነውን? ይህንን ካላችሁ ጥመታችሁ ግልፅ ወጣ አለያ ወደነሱ መንገድ ተመለሱ!!

3) ይህ የተምታታ ግንዛቤ መነሻ ያደረገውን ሀሳብ ስንመለለት፤ ክርስቲያኖች የኢሳን ልደት በማክበራቸው አላህን በማመስገን ከምርጦቹ የሰለፎች ትውልዶች መቅደማቸውን ያመላክታል።
ይህ ደግሞ ባጢል ነው!!

4) አልሐበሺ እና ተከታዮቹ ክርስቲያኖችን በመከተል ልደት ሲያከብሩ መልእክተኛው ﷺ በብዙ ሀዲሶች፤ በኢስላማዊ እንድንኮራ ማዘዛቸውና አይሁዶችና ክርስቲያኖችን አርአያ እንዳናደርግ አበክረው መምከራቸውን ለምን ዘነጉ? ሙስሊም ከካፈር ጋር መመሳሰል እንደሌለበት አያውቁምን??

መልዕክተኛው ﷺ እንዲህ ብለዋል፤

عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيّ، قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللّهِ صلى الله عليه وسلم "لَتَتّبِعُنّ سَنَنَ الّذِينَ مِنْ قَبْلِكُمْ. شِبْراً بِشِبْرٍ، وَذِرَاعاً بِذِرَاعٍ. حَتّىَ لَوْ دَخَلُوا فِي جُحْرِ ضَبَ لاَتّبَعْتُمُوهُمْ" قُلْنَا: يَا رَسُولَ اللّهِ آلْيَهُودُ وَالنّصَارَىَ؟ قَالَ "فَمَنْ؟".
[رواه البخارى ومسلم ].

አቢ ሰዒድ አልኹድሪይ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ አሉ፤ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ፤ «ከናንተ በስተፊት የነበሩትን (ህዝቦች) ፈለግ ስንዝር በስንዝር እርምጃ በእርምጃ ትከተላላችሁ። የተሳቢ እንስሳ ጉድጓድ እንኳ ቢገቡ ትከተሏቸዋላችሁ!»

የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ሆይ ይሁዶችንና ነሳራዎችን ነው ? «ሌላ ማንን ነው!» (እነሱን ነው እንጂ) አሉ።

ይህንን ነብያዊ ትንቢት ባንሰማ ኖሮ በሙዘፈር ድርጊት ተገርመን አናበቃም ነበር።

5) አላህ ዲናችንን የተሟላ አድርጎት ሳለ፤ ክርስቲያኖች ሰሩት ብለን በዲናችን የሌለን ነገር እንፈፅማለን??

(ٱلْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِى وَرَضِيتُ لَكُمُ ٱلْإِسْلَـٰمَ دِينًۭا ۚ فَمَنِ ٱضْطُرَّ فِى مَخْمَصَةٍ غَيْرَ مُتَجَانِفٍۢ لِّإِثْمٍۢ ۙ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌۭ رَّحِيمٌۭ) المائدة 3

«ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለእናተ ሞላሁላችሁ። ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ። ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ»
አልማኢዳህ 3

በእውነትም የዛኔ ዲን ያልነበረ አሁን ዲን ሊሆን አይችልም!!

አኹኩም አቡጁነይድ
ረቢኡልአወል 9 /1436 ዓ.ሒ

https://t.me/abujunaidposts