🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

#ህይወት_እንደወረደ ለዕረፍት ቀናቶች የሚሆን አዲስ #ቀደዳዎች ናቸው። አንድ ነገር ግን አምናለው። | SAFE LIGHT INITIATIVE

#ህይወት_እንደወረደ
ለዕረፍት ቀናቶች የሚሆን አዲስ #ቀደዳዎች ናቸው።
አንድ ነገር ግን አምናለው። ሁላችንም የኮንትራት ኑሮ በምንኖርባት በእዚህች አጭር ህይወት ስንቱን ለመሆን ስንጣጣር ግርም ይለኛል። ሁሉ ከንቱ የከንቱ ከንቱ እንደሆነ ሁልህም ታውቃለህ። መቼ ታዲያ ከመባዘን አተረፈህ። ማግኘትም ማጣትም፣ መውደቅም መነሳትም፣ ስቃይም እረፍትም ትርጉም ሚኖራቸው እኮ አንተ ስትኖር ነው። አሁን ሞትኩለት ያልከው ነገር አንተ ላይ ህይወት ሚኖረው እስትንፋስህ እስካለ እንደሆነ ብታቅ ምነኛ እንዲህ ባልባዘንክ ነበር። እናማ በእዚህች በአውሎ ንፋስ ውስጥ እንዳለ የበራ ሻማ ለሆነው ህይወትህ ይህን ያህል እየተጨነቅህ ምን ታተርፋለህ። እምልህ አትኑር አይደለም በቃ በቀንህ ላይ ትንሽዬ በሰዎች ህይወት ላይ አዋጣ፣ በማግበስበስ ሳይሆን በማካፈል ኑር፥ በቃ ብዙ አታካብድ ያለህን አጣጥም፥ ካሌለህ የለህም አልቅስ ተናደድ ከዛ እንባህን አብሰህ ስሜትህን እንደሚገባ አስተናግደህ ደግሞ ተነስ። በቀንህ መጨረሻ እንደው ቀንህን መለስ ብለህ ስታየው የሆነ አንድ መልካም ነገር ከሰራህ፥ የመልካም ነገር እንጂ የጥፋት ምክንያት አለመሆንህ፣ የእረፍት እንጂ የስቃይ ምክኒያት አለመሆንህ፣ የመፍትሄ እንጂ የምሬት ምክኒያት አለመሆንህን አስበህ ፈጣሪህን አመስግንና ፈገግ ብልህ ተኛ። ደግሞ ስትወድቅ እንዴት ብለህ አትማረር። ላትወድቅ ነው ታዲያ? እየኖርክ ያለኸው እኮ መንግስተ ሰማያት አይደለም። ብዙ ለጭብጨባ አትኑር፥ ለሰዎች ተቀባይነት ከኖርክ እንግዲያውስ የተዉህ ግዜ መሞትህ ነው። ሰጪ ከሆንክ ብዙ ለመቀበል አትሽቀዳድም። በቃ ማድረግ የቻልከው ካንተ ቸሮታ ሳይሆን እድል ስላገኘህ ነው። ስንቶች መስጠት እንደሚፈልጉ ግን እድል አጥተው እንደሚቆጩ ብታውቅ አትታበይም። በማድረግህ ብዙ እውቅናን አትጠብቅ። እምልህ በጣም ብዙ ያደረኩ የመሰለኝ ግዜ ሰዎች ሲያወሩት በጆሮዬ መስማት ያስደስተኛል። ድንቄም አድራጊ። ብዙ አልጠቀመኝም። ፈገግ በል እስቲ። የብዙዎቻችን ውበት እኮ ፈገግታችን ላይ ነው። አሁን ይሄን ስል ምን ሚያስደስት ዜና እያለ ነው ፈገግ ምለው እንደውም የፕሮፋይል ፒክቸሬን መቀየር ነው ያለብኝ ምትል እንደምትኖር አስባለው ግን በቃ ሀዘን በመጽናናት ውስጥ አዋጥቶ አያቅም። ፈገግታ ግን መልካም ወዳጅህ ነው። ያፅናናሃል! ሰው ሁሉ በሚንጋጋበት ግር አትበል። በምክኒያት ብቻህን ውደቅ እንጂ በአላዋቂ የመንጋ ስኬት ያለምክኒያት አትጨፍር። ቀንህ ላይ አዕምሮህን ስራ አታስፈታው። ያለማቋረጥ ጠይቀው።
የሰዎችን ስህተት ከነፍሳቸው ንፅህና ለይተህ ተመልከት። ፈራጅ አትሁን ለምን መሰለህ በፈረድከው ልክ ትፈተናለህ። ስትወድቅ ፀፀቱን አትቋቋመውም። በትላንት ስህተትህ ዛሬ ላይ ታስረህ ነገህን አታበላሽ። ከዛ በቃ ህይወት ከባድ ነች እያልክ ሙሾ እያወጣህ አትኑር። ሁሉም ነገር ከባድ ነው አንዱን ከባድ ወስንና ተቀብለህ ኑር።
ይመቻቹ።
#መልካም_የዕረፍት_ቀናት
#InspireEmpowerTransform
@SafeLightOfficial