🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ሰው ሰውን ሲገድል በንዴትና በቁጭት ብዙ እንናገራለን። ሰው ራሱን ሲያጠፋ እጅግ እናዝናለን። ሰው | SAFE LIGHT INITIATIVE

ሰው ሰውን ሲገድል በንዴትና በቁጭት ብዙ እንናገራለን። ሰው ራሱን ሲያጠፋ እጅግ እናዝናለን። ሰው በሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ ሞት ካጠገባችን ድንገት ሲለይ ፈጣሪዬ አሟሟቴን አሳምርልኝ በማለት ፈጣሪን እንማፀናለን።
ሰው ፈጣሪ የሰጠውን ድንቅ አዕምሮ ሳይጠቀም በቁሙ ሲሞትስ ምን ይባላል? ሰው ሀብቱ ላይ ተቀምጦ ሲለምን ስታይ ምን አይነት ሞት ሞተ ብለህ ትናገራለህ? ሰው እንጀራው ላይ ተቀምጦ ሲራብ፣ ሰላምን ሸጦ ጦርነት ሲፈልግ፣ ድህነት ተመችቶት ባለጠግነትን ሲገፋ፣ በምሽት ገንዘብን ሲያማ አድሮ በጠዋት ገንዘብ ፍለጋ ሲንከራተትስ? ሀብታም ሀጥያተኛ ድሃ ድግሞ ፃድቅ አድርጎ ሲደመድምስ? የሌሎች ጥሩ የራሱ ውዳቂ አድርጎ በዝቅተኝነት ስሜት እየተሰቃዩ መኖርስ?
ሁላችንም ሙኣቾች ነን፥ የህይወት ጎሉ ለዘላለም መኖር አይደለም። ከመቃብርህ በላይ ከሌሎች ጋር አብሮ የሚኖር አንድ ነገር ትተህ ማለፍ ግን ትልቅ የህይወት ግብ ነው።
ታዲያማ ሀገሬን ስመለከታት በወንጀለኞች ተሞልታ ተመለከትኳት። አዕምሮን ካለመጠቀም በላይ ምን ወንጀል አለ? ሀገሬ በሀጥያተኞች ተጨንቃ ተመለከትኳት፥ ድህነት ተመችቶት እንደመኖር የመሰለ ምን ሀጥያት አለ? ልብ አድርጉልኝ፥ ደሃ መሆን ሀጥያት ነው እያልኩኝ አይደለም። ድህነትን ለማሸነፍ አለመሞከርና ከድህነት ጋር ተመቻችቶ መኖር፣ ፈጣሪ የሰጠህን ትልቅ አዕምሮ እንደምናምንቴ በመቁጠር መኖር ግን ሰጪውን መናቅ ነው። ድፍረትና ሀጥያት ነው። ደሀ ሆነህ ልትወለድ ትችላለህ። የአንተ ስህተት አይደለም። ከእሱ ጋር ግን እኔ ትብስ አንተ ትብስ ተባብለህ መኖርና መሞት ግን ትልቅ ስህተት ነው። በቁም ሞተህ ነበር ማለት ነው።
ባለጠግነት ሁለንተናዊ ሀብት ነው። #በጭንቅላት #በልብና #በእጅ። ጭንቅላትህ ችግር ፈቺ ዕውቀትን ሲሰበስብና ችግር ስፈታበት፣ በዕውቀትህ ብቻ እንዳትታበይና ሰውን አሳንሰህ እንዳትመለከት ደግሞ በልብህ ትሁት እንድትሆን ስትፈቅድ፣ በመጨረሻም እጆችህ ሰራተኛና ሞካሪ ሆነው ገንዘብ እንዲሰሩ፥ በእንቅልፍህ ድህነት ቤቱን እንዳይሰራብህ ቆራጥ ስትሆን ያን ጊዜ የባለጠግነት ትኬቱን ቆርጠሀል ማለት ነው።
ምርጫው ያንተ ነው። ህይወት ምትጣፍጠው ከሂደቱ ጋር ነው። ባቋራጭ መክበር ትችላለህ ባለጠጋ ግን አይደለህም። ታዲያ ምን ታስባለህ? ምርጫው ያንተ ነው።
ቸር እንሰንብት!!!
#InspireEmpowerTransform
@SafeLightOfficial