🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ቅድሚያ ለትልቁ (Prioritizing) መምህሩ ወደ ክፍል ትልቅ ጠርሙሰ እና ትልቅ የኘላስቲክ ከ | SAFE LIGHT INITIATIVE

ቅድሚያ ለትልቁ (Prioritizing)

መምህሩ ወደ ክፍል ትልቅ ጠርሙሰ እና ትልቅ የኘላስቲክ ከረጢት ይዞ ገባ። "ዛሬ ለሕይወታችሁ በእጅጉ የሚጠቅም ትምህርት ስለ ጊዜ ትማራላችሁ" አለ ትልቁን ጠርሙስ ጠረጴዛ ላይ እያስቀመጠ። ከዚያም ድንጋዮች ከቀረጢቱ ውስጥ አውጥቶ ጠርሙሱ ውስጥ ሞላ። "ተማሪዎች ጠርሙሱ ሞልቷል?" ብሎ ጠየቀ ተማሪዎቹም "አዎ!" አሉ በአንድ ድምፅ። ቀጥሎም አነስ ያሉ ጠጠሮችን አውጥቶ እዛው ጠርሙሱ ውስጥ መጨመር ጀመረ። በመሀል ጠርሙሱን ይነቀንቀዋል ጠጠሮቹም በድንጋዮቹ መሀል እያለፉ ከታች ጀምሮ ጠርሙሱን ሞሉት። "አሁንስ ሞላ?" አላቸው መምህሩ "አዎ" አሉ ተማሪዎቹ ትንሽ ግራ በመጋባት። መምህሩም በድጋሚ ደቃቅ አሸዋ ጠርሙሱ ውስጥ ይሞላ ጀመር። አሸዋውም በድንጋዮቹና በጠጠሮቹ መሀል ባለው ክፍተት በመግባት ጠርሙሱን ሞላው። "አሁንስ ሞላ?" አለ መምህሩ። ክፍሉ ዝም አለ። እንደገና መምህሩ ውሀ በጠርሙሱ ውስጥ መሙላት ጀመረ። ውሀውም ከታች እስከ ላይ ጠርሙሱን ሞላው።