🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

አቶ አብነት ገ/መስቀል ከሚድሮክ ኢትዮጵያ ግሩፕ ሃላፊነታቸው ተነሱ! ለረዥም ጊዜ በሚድሮክ ኢትዮ | Crazy jocks 😜😂

አቶ አብነት ገ/መስቀል ከሚድሮክ ኢትዮጵያ ግሩፕ ሃላፊነታቸው ተነሱ!

ለረዥም ጊዜ በሚድሮክ ኢትዮጵያ በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች የሰሩትና ከ1 አመት በፊት የቀድሞው ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አረጋ ይርዳው ከስልጣናቸው ከተነሱ በኃላ እሳቸውን ተክተው የነበሩት አቶ አብነት ገ/መስቀል ከሃላፊነት ተነስተዋል። አቶ አብነት ስልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው እንደለቀቁ ለፎርቹን ቢናገሩም በእሳቸው ቦታ እደተተኩ የተናገሩት አቶ ጀማል አህመድ ግን የሚድሮክ ኢትዮጵያ ባለቤት የሆኑት ሼህ ሁሴን መሃመድ አል አሙዲን ከስልጣን እንዳነሷቸው ተናግረዋል።እንደ አቶ ጀማል ገለፃ አቶ አብነት ከሃላፊነት የተነሱት ሃላፊነታቸውን በአገባቡ ባለመወጣትና እምነትን በማጉደል በሚሉ ምክንያቶች ነው። በዚህ ዙርያ ተጨማሪ መረጃ ከአቶ አብነት ማግኘት እንዳልቻለ ጠቅሶ የዘገበው አዲስ ፎርቹን ነዉ።