🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስር የሚገኘው አንጋፋው ንግድ ሥራ ኮሌጅ በ15 ቀናት ውስጥ ግቢውን ለቆ | Crazy jocks 😜😂

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስር የሚገኘው አንጋፋው ንግድ ሥራ ኮሌጅ በ15 ቀናት ውስጥ ግቢውን ለቆ እንዲወጣ እንደተወሰነበት ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር ኮሌጁ ግቢውን እንዲለቅ ቀነ ገደብ የሰጠው፣ መንግሥት ግቢውን ለትላልቅ ፋይናንስ ተቋማት ግንባታ ፈልጎታል በሚል ነው። የኮሌጁ አስተዳደር በበኩሉ የ80 ዓመታት ዕድሜ ያለው ኮሌጁ የፋይናንስ ሙያተኞችን ለዘመናት ሲያፈራ መኖሩን በመጥቀስ፣ ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በቅርበት እየሰራ መቀጠል እንጅ ግቢው መፍረስ የለበትም በማለት ውሳኔውን ተቃውሟል ተብሏል።