Get Mystery Box with random crypto!

አቶ ስብሐት ነጋ ወ/ ሮ ኬሪያ ኢብራሂምን ጨምሮ በሽብር ወንጀል የተከሰሱ 19 ተከሳሾች ፍርድ ቤት | Crazy jocks 😜😂

አቶ ስብሐት ነጋ ወ/ ሮ ኬሪያ ኢብራሂምን ጨምሮ በሽብር ወንጀል የተከሰሱ 19 ተከሳሾች ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ እንዲደርሳቸው ተደረገ፡፡

በማረሚያ ቤት የሚገኙት አንባሳደር አባይ ወልዱና ዶ/ርአስገዶም ተስፋዬ ያልቀረቡ ሲሆን 19 ኙ ግን በችሎት ተገኝተዋል፡፡

ያልቀረቡት ቀሪዎቹ እነ ዶ/ር ደብረጺኦን ፡ጌታቸው ረዳ፡ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ( ሞንጆሪኖ) ጨምሮ 41 ተከሳሾችን ፖሊስ አፈላልጉ ለማቅረብ በትግራይ ክልል ካለው ፀጥታ ችግር አንፃር እንደሚቸገር መግለጹን የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብርና የህገመንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት አብራርቷል፡፡

ነገር ግን በችሎት የተገኙ ተከሳሾች የመኖሪያ አድራሻቸውን፡ የትዳር ሁኔታቸውን እና የስራቸውን ደረጃ አጠቃላይ ማንነታቸውን ለፍርድ ቤቱ አስመዝግበዋል፡፡