Get Mystery Box with random crypto!

ነገ በአ/አ የሚዘጉ መንገዶች ! የታላቁ የሩጫ ውድድር ምክንያት የሚዘጉ መንገዶች ፦ - ኮቦሌ | Weight360

ነገ በአ/አ የሚዘጉ መንገዶች !

የታላቁ የሩጫ ውድድር ምክንያት የሚዘጉ መንገዶች ፦

- ኮቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ህንፃ

- ከጎተራ ማሳለጫ ወደ መስቀል የሚወስደው መንገድ የቀድሞ አራተኛ ክፍልጦር

- ከቡልጋሪያ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚወስደው ኬኬ ህንፃ ወይም ጨርቆስ ማዞሪያ

- ከሳር ቤት ወደሜክሲኮ ለሚመጡ አፍሪካ ህብረት አደባባይ

- ከካርል አደባባይ ወደከፍተኛ ፍ/ቤትየሚወስደውመንገድ ልደታ ፀበል

- ከጦርኃይሎች ወደ ሚክሲኮ ለሚመጡ ኮካ መገንጠያ ሜክሲኮ ለሚመጡ ጆስሐንሰን

– ከመርካቶ በጎማ ተራ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚመጡ በርበሬበረንዳ

- ከተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በጎማ ቁጠባ የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኋላ በር (ሼልድሬንስ)

- ከቸርቸር ወደ አምባሳደር ፣ ሜክሲኮ እና ለገሃር ለሚመጡ ቴድሮስአደባባይ

- ከአዋሬ ወደ ካዛንቺስ ለሚመጡ ሴቶች አደቤይ

- ከመገናኛ ወደ 22 ለሚመጡ ዘሪሁን ህንፃ

- ከቦሌ መድኃኒያለም የሚመጡ አትላስ ሆቴል አካባቢ

ለተሽከርካሪ ዝግ ሲሆኑ በተጨማሪም ከውስጥ ለውስጥ መንገዶች ተወዳዳሪዎቹ ወደሚያልፉባቸው መንገዶች መውጣት በጥብቅ የተከለከለ ነው።

አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንድትጠቀሙ መልዕክት ተላልፏል።

በተጨማሪም ወድድሩ በሚካሄድባቸው መንገዶች ከማለዳው 11 ሰዓት ከ 30 ጀምሮ ተሸከርካሪን ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ማቆም የተከለከለ ነው።

አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥም ሆነ ለፖሊስ መረጃ ለመስጠት 011-1-11-01 11 እና በ991 ነፃ የስልክ ቁጥሮች መጠቀም ይቻላል። ~ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን