Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት ናችሁ የዶሮ_ላባዎች_ሲበተኑ አንድ ወጣት ወደ አ | ❿ⓉⒽ 🅕🅤🅝 ™

ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት ናችሁ

የዶሮ_ላባዎች_ሲበተኑ

አንድ ወጣት ወደ አንድ ታላቅ አባት ዘንድ ይሄድና "አባት እውነት ባልሆነ አሉባልታ የሰውን ስም በማጥፋት የጎዳሁ መሆኔ አሁን ታወቀኝ። እና ስለ ሀጢያቴ ምን ላድርግ?" ብሎ ጠየቃቸው።

እኛም ጥበበኛ አባት "የዶሮ ላባ ፈልገህ ሰብስበህ አምጣ" አሉት። ሄዶ ሰብስቦ ይዞ መጣና "ይኸው" አላቸው። "ሂድና በአሉባልታ ወሬ በጎዳሀቸው ሰዎች በር ላይ አስቀምጠው" አሉት።

እሱም ሄዶ አስቀምጦ መጣና ያሉኝን "አድርጌያለው" አላቸው። ከዛ እሳቸውም "በል ሂድና ያስቀመጥከውን ላባ ሰብስበህ አምጣ" አሉት። እሱም "እንዴ ይሄማ አይሆንም፤ ይሄኔ ንፋስ በትኗቸዋል" አላቸው።

እሳቸውም "አየህ ልጄ ልክ እንደዚህ አንተ የበተንከው የሀሜትና አሉባልታ ወሬ በከተማ ሁሉ ስለ ተሰራጨ መልሶ መሰብሰብ ከባድ ነው" በማለት ከመለሱለት ቡሃላ "አየህ ሀሜተኛ አትሁን። ዳዊት 'አቤቱ ለአፌ ጠባቂ አኑር' እንዳለው ጠባቂ በሌለው ምላስ በሀሜት ትዳራቸው የፈረሰ ፣ ቢዝነሳቸው የከሰረ ፣ ትምህርታቸውን ያቋረጡ ፣ ከሚወዱት ሰው የተለዩ ፣ ከቤተክርስቲያን አገልግሎት የሀሜትን ጦር ፈርተው የራቁ ብዙዎች ናቸው። ሀሜተኞችና አሉባልታ አውሪዎች የሚያጠፉት ጥፉት እሳትና ሰይፍ ከሚያጠፉት ይበልጥ ፈጣንና አደገኛ ነው።

ሀሜተኛ ምላስ በክፉ ጠባዩ አያሌዎችን የገደለ ብዙዎችን የደም እንባ ያስለቀሰ መልካም ኑሮን ያናጋ መርዘኛ እባብ ነው። ብዙዎች በሀሜተኛ ምላስ ጅራፍ ተገርፈው ቆስለው ደምተዋል። ሀሜተኞች ወላጅና ልጅን ወንድምና እህትን ፣ ባልና ሚስትን ፣ አሰሪና ሰራተኛን አቃቅረው አጣልተዋል።"

ስለዚህ እስቲ እራሳችንን እንመርምር ስለምናወራው ነገር እንጠንቀቅ፡፡


ለፅሁፉ ላሊ ናዙን እናመሰግናለን

መልካም ቀን፤ ቸር ወሬ ያሰማን

Kogoese
⓾𝕥𝕙 𝕗𝕦𝕟 𝕥𝕙𝕖 𝕓𝕖𝕤𝕥 𝕨𝕒𝕪 𝕠𝕗 𝕝𝕖𝕒𝕣𝕚𝕟𝕘