Get Mystery Box with random crypto!

#ሞል ሞሎች ጉድጓድ በመቆፈር ችሎታቸው ነው የሚታወቁት። ጥፍሮቻቸውም እረጃጅምሞች እና ለ | ❿ⓉⒽ 🅕🅤🅝 ™

#ሞል
ሞሎች ጉድጓድ በመቆፈር ችሎታቸው ነው የሚታወቁት። ጥፍሮቻቸውም እረጃጅምሞች እና ለ ቁፋሮ ምቹ ናቸው። በ መሬት ውስጥ ለውስጥ እየቆፈሩ በሚሄዱበት ወቅት የ ኦክስጅን እጥረት አያጋጥማቸውም ምክንያቱም ሳንባቸው አንድ ጊዜ የሳበውን ኦክስጅን 100% ሳያባክን የመጠቀም ችሎታ ስላላቸው በትንሽ ኦክስጅን ረጅም ሰከንዶች መቆየት ይችላሉ። የሚመገቡት በመሬት ውስጥ የሚገኙ ትሎችን ነው።የሞል ምራቅ መርዛማ ነው። ምራቁን መሬት ላይ በመትፋት በ ምራቁ በኩል የሚያልፉ ትሎችን ፓራላይዝ ያደርጋቸው እና በቀላሉ ይዞ ይመገባቸዋል።
ሞሎች ትሎችን ከመብላታቸው በፊት በ እጃቸው በመያዝ ከ ትሎቹ ላይ ቆሻሻዎችን አንስተው ይጥላሉ።
ሴት ሞሎች ለ 42 ቀናት አርግዘው ነውየሚወልዱት። በ አብዛኛው ከ 3 እስከ 5 ልጆች ይወልዳሉ።
የተወለዱት ልጆች ከ 30 እስከ 40 ቀን ድረስ እንክብካቤ ከተደረገላቸው በኋላ ሌላ ቦታ የራሳቸውን ኑሮ ይመሰርታሉ።