🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ኮኮቦች ሲደበሩ episode 3 »» ኤሪስ፦ ሲደበሩ በተቻላቸው አቅም ዘና ለማለትና ለመስከን ይሞ | ❿ⓉⒽ 🅕🅤🅝 ™

ኮኮቦች ሲደበሩ episode 3

»» ኤሪስ፦ ሲደበሩ በተቻላቸው አቅም ዘና ለማለትና ለመስከን ይሞክራሉ፣ ሻዎር መግባት ከገቡ ቧለ ለረጅም ግዜ ይቆያሉ፣ እያሰቡ ወይ
በአረፋው እየተጫወቱ ሊሆን ይችላል፣ ከዛ ቧላ ድምፁን ከፍ አድርገው ዘፈን ቢሰሙ ይወዳሉ።

»» ቶረስ፦ እረፍት ማድረግ ከልፈለጉ በቀር ቶረሶች ሲደብራቸው፣ ቲቪ ወይም ሌላ ነገር መስማት አይፈልጉም፣ ያሉበትን ክፍል በማፅዳትና እቃዎችን በማስተካከል ያሳልፋሉ።

»» ጄሚናይ፦ ፈጣኖቹ ጄሚናዎች ድብርት ውስጥ ሲገቡ፣ ፊልም ያያሉ ወይ ፕላን ያደርጋሉ፣ ፖፕኮርን፣ ከረሜላ ብቻ ሚፈልጉትን ነገር ይበላሉ፣ በአቅራቢያቸው ያለ ሰው ጋ ይደውላሉ፣ እነሱን ካጡ ሳይገናኙ ለብዙ ግዜ የተረሳሱት ሰው ጋ ይደዋወላሉ፣ ያገኛሉ።

»» ካንሰር፦ ከቤት አይወጡም፣ ቤታቸው ባለው ነገር ፈታ ለማለት ያስባሉ ፣ ወይ ለመተኛት ይሞክራሉ።

»» ሊዮ፦ ሲጀምር ሊዮዎች አንድ ቦታ ደባሪ እስኪሆን ድረስ አይታገሱም፣ ድብርት ውስጥ ከገቡ ግን አብዛኛውን ግዜ ከራሳቸው ጋ ያሳልፋሉ፣ ሾው አፕ ምናምን በማድረግ

»» ቪርጎ፦ ብዙ ግዜ ሚሰሩትን አያጡም፣ የሆነ ነገር ላይ ነው ሚሆኑት፣ አዛ ከሆኑ ግን ቤት ውስጥ ሚስታካከሉ ነገሮችን ማስተካከል ይጀምራሉ፣ ሚስተካከል ቢጠፋ እንኳን ድጋሚ አበላሽተው ያስተካክላሉ።

»» ሊብራ፦ ሊብራዎች ሲደበሩ ሚያደርጉት ነገር ግራ የገበው ነገር ነው፣ ያስቃል። ከበሰባቸው ግን መነጫነጭ ያበዛሉ፣ ባገኙት ነገር ላይ ቅሬታ ማቅረብ ይጀምራሉ።

»» ስኮርፒዮ፦ የሆነ ቦታ ቁጭ ብለው እጃቸውን በመፈተል፣ ስለ ሆነ ነገር ያስባሉ፣ ሮጥ ሮጥ ብለው ስፖርት ቢሰሩም ደስ ይላቸዋል።

»» ሳጁታሪየስ፦ ብዙ መተኛት ይፈልጋሉ፣ ስንፍናቸው ተጨምሮበት ሙሉ ቀንም ቢሆን ይመርጣሉ፣ ካልሆነ በምናባቸው በሚስሉት ረጃጅም የጉዞና የሕይወት መንገድ በመመሰጥ፣ ካሉበት ድብርት ለመውጣት ይሞክራሉ፣ በመጨረሻም ረጅም መንገድ ወክ ያደርጋሉ።

»» ካፕሪኮርን፦ ሚሰሩት ነገር ካላጡ በቀር አይደበሩም፣ ከተደበሩ ግን በድብቅ ወይ የኤክሳቸውን ፕሮፋይል ይጎረጉራሉ፣ ወይ የሆነ ነገር በማሳስና በመፈለግ ይደበራሉ።

»» አኳሪየስ፦ ዩቲዩብ ላይ አስቂኝ ቪዲዮ ያያሉ፣ ቴሌግራም ይገባሉ ይወጣሉ፣ ፌስቡክ ይገባሉ ይወጣሉ፣ አሁንም ቴሌግራም ይገባሉ ፕሮፋይል ይቀይራሉ ወይ ያጠፋሉ ወይ ደግሞ የሰው ያያሉ፣ አሁንም ይወጣሉ፣ ዘፈን ይከፍታሉ፣ ይቀይራሉ........

»» ፓይሰስ፦ ፓይሰሶች ሙዚቃ ይወዳሉ ብቻ ሳይሆን ብዙ ነገራቸው ነው፣ ሲዳብራቸውም ብዙ ግዜ ሙዚቃ ይሰማሉ፣ ከዛ ወይ ይተኛሉ፣ ወይ ትክዝ ይላሉ።