🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

#ብዙ_መጻሕፍት_የተሸከመች_አህያ_ያው_አህያ_ናት! የሱፊ ተረት እንዲህ ይላል፦ 'ብዙ መጻሕፍት | ❿ⓉⒽ 🅕🅤🅝 ™

#ብዙ_መጻሕፍት_የተሸከመች_አህያ_ያው_አህያ_ናት!

የሱፊ ተረት እንዲህ ይላል፦

"ብዙ መጻሕፍት የተሸከመች አህያ ያው አህያ ናት!"

ይቺን አህያ ሁላችንም እናውቃታለን። ቀኑን ሙሉ ተዘፍዝፎ የሚያነብ ምሁር፣ ባዶ ቃላት የሚሰብክ ሰባኪ ወይም ምንም የማይሰራ አንባቢ ሊሆን ይችላል። እውነተኛ ጥበብ የሚገኘው ቁምነገሩን በማንበብ ሳይሆን ቁምነገሩን በመኖር ነው።

ቅዱሳን መጻሕፍትን አንብበናል፤ ግን ምሳሌውን ተከትለን በፍቅር አልኖርንም። የሳይንስ ሰነዶችንም አገላብጠናል። ለምስኪኑ ወገናችን ጠብ የሚል ነገር አልፈጠርልነትም።

በቤተክርስቲያን እና በመስጊድ እንመላለሳለን፤ ቅዱስ ቃሉን ከመጣፍም ከሊቅ አፍም እንሰማለን። ግን በልባችን ፍቅርና ርህራሄ የለንም። ያነበብነውን የማንኖር ግብዞች ሆነናል።

dotcomtvshow