🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

አልበርት አንስታይን የrelativity theoryን ለሳይንስ ካበረከተ በኋላ በተለያዩ የአሜሪካ ዩ | ❿ⓉⒽ 🅕🅤🅝 ™

አልበርት አንስታይን የrelativity theoryን ለሳይንስ
ካበረከተ በኋላ በተለያዩ የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች
እየተዘዋወረ ሌክቸር ይሰጥ ነበር፡፡ በሄደበት ቦታ ሁሉ
አብሮት የመሚዞር ሀሪ የተባለ ሹፌርም ነበረው፡፡ ሀሪ
እንያንዳንዱን ሌክቸር ሲከታተል ኖሯል፡፡
አንድ ቀን ከሌክቸር በኋላ ሀሪ “ፕሮፌሰር አንስታይን፤ የ
relativity ሌክቸሮችህን ለበርካታ ጊዜያት ተከታትያለሁ፡፡
እድሉ ቢሰጠኝ ያለምንም እንከን እንደማቀርበው
እርግጠኛ ነኝ” አለው፡፡ አንስታይንም “በጣም ጥሩ፡፡
እንግዲያውስ በሚቀጠውለው ሳምንት ወደ ዳርትማውዝ
እናቀናለን፡፡እዚያ ማንነቴን ጠንቅቀው ስለማያውቁ እኔን
መስለህ ማቅረብ ትችላለህ፡፡ እኔም ሀሪ እሆናለሁ፡፡”
እንደታሰበው ሀሪ ያለምንም ስህተት በግሩም ሁኔታ
ትምህርቱን አደረሰ፡፡ አንስታይንም ሹፌሩን መስሎ
ሲከታተል ቆየ፡፡ ልክ በንግግሩ መጨረሻ ላይ አንድ
ተመራማሪ የተወሳሰበና ለመመለስ ጥልቅ የሂሳብ
እውቀት የሚጠይቁ ጥያቄዎችን አዥጎደጎደበት፡፡
ሀሪም በዚህ ጊዜ “የዚህ ጥያቄ መልስ እጅግ በጣም
ቀላል ነው፡፡ ስለሆነም ሹፌሬ እንዲመልሰው እድሉን
ልስጠው፡፡” አለ ይባላል፡፡