🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

#ገና ከመወለዱ ሱስ አስቸገረው! ሲወለድ ክብደቱም ሆነ ጤንነቱ ኖርማል ነው። ድንቡሽቡሽ ያለ ነው | ❿ⓉⒽ 🅕🅤🅝 ™

#ገና ከመወለዱ ሱስ አስቸገረው!

ሲወለድ ክብደቱም ሆነ ጤንነቱ ኖርማል ነው። ድንቡሽቡሽ ያለ ነው። በሁለተኛው ቀን "እሪ" ብሎ ማልቀስ ጀመረ። እናቱ ብታባብለው ብታባብለው ለቅሶው አልቆም አለ። በተደጋጋሚ አስመለሰው። ላብበላብ ሆነ። ሰውነቱ መንቀጥቀጥ ጀመረ። ሀኪሞቹ ያሉትን ምርመራዎች ሁሉ ቢሰሩለትም ምንም ሊገኝ አልቻለም። እናቱንም መመርመር ጀመሩ። ከዛ እሷ ሄሮይን የተባለው ዕፅ ሱሰኛ እንደሆነች ደረሱበት።
ለካ ህፃኑ ማህፀን ውስጥ እያለ እናቱ ሄሮይን ስትጠቀም እሱም በደሟ አማካኝነት ይደርሰው ነበር። ከተወለደ በኋላ ግን ወተት ውስጥያለው የሄሮይን መጠን በጣም ዝቅተኛ ስለሆነ የለመደውን አላገኘም። ገና ከመወለዱ ሱስ አስቸገረው።

እናቶች የሚወስዷቸው ሱስ አስያዥ ነገሮች (ከቡና ጀምሮ) ከእነሱ አልፎ ልጆች ላይም ተፅእኖ እንደሚያደርስ አስታውሶ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። ሱስ የሚታከም የአእምሮ ህመም ነው የሚባልውም በምክኒያት ነው።

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው