ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለሚቀበላቸው ተማሪዎች አስፈላጊውን የደህንነት ጥበቃ እንደሚያደርግ ገለፀ፡ | Tikvah-University

Picture 1 from Tikvah-University 2024-01-09 11:08:29
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለሚቀበላቸው ተማሪዎች አስፈላጊውን የደህንነት ጥበቃ እንደሚያደርግ ገለፀ፡፡

ዩኒቨርሲቲው ለ2016 የትምህርት ዘመን ከጥር ወር ጀምሮ 11 ሺህ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊ የሆኑ የመመገቢያና ማደሪያ ክፍሎች እንዲሁም በቤተ- መጽሐፍትና በሌሎች አገልግሎት መስጫ ስፍራዎችም ዝግጅት ማድረጉን የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ይኸይስ አረጉ (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

"በክልሉ በሚፈጠር የፀጥታ ችግርና የመንገድ መዘጋት ለዩኒቨርሲቲው የሚያስፈልገው የምግብና የቁሳቁስ ግብዓት እጥረት እንዳያጋጥም አስፈላጊው ጥረት ይደረጋል" ብለዋል።

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለነባር እና አዲስ የቅድመ እና ድህረ-ምረቃ ተማሪዎቹ ከጥር 16/2016 ዓ.ም ጀምሮ ሪፖርት ማድረጉ ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ ( ጥሪው፦ https://t.me/TikvahUniversity/9834)

@tikvahuniversity
Tikvah-University

Tikvah-University

@tikvahuniversity
380.83K Subscribers
Education Category