Get Mystery Box with random crypto!

አንዱ ለአዲስ ዓመት ከገርልፍሬንዱ HNY የሚል ሜሴጅ በሞባይል ስልኩ ይደርሰዋል። ወዲያውኑ ይደው | ✍ወግ እና ቀልድ ✏

አንዱ ለአዲስ ዓመት ከገርልፍሬንዱ HNY የሚል ሜሴጅ በሞባይል ስልኩ
ይደርሰዋል።

ወዲያውኑ ይደውልላትና፦ “ፍቅሬ HNY የሚለው መልዕክትሽ ደርሶኛል
ምን ማለት ነው?” ይላታል

እሷ፦ በጣም እየሳቀችበት... አንተ ጌጃ ነህ እንዴ?! ለማንኛውም HNY
ማለት Happy New Year ማለት ነው፤ በአማርኛ መልካም አዲስ ዓመት እንደማለት።

ይበሳጭና ጆሮዋ ላይ ስልኩን ዘግቶ ወዲያው በአማርኛ “መ.ድ.ያ” የሚል
መልእክት ይልክላታል።

ከደቂቃዎች በኋላ መልሳ ትደውላለች።
እሷ፦ አንተ ጌጃ “መ.ድ.ያ” ብለህ የላከው ሜሴጅ ደሞ ምን ማለት ነው?
ስለተበቀላት ደስ ብሎት እየሳቀ፦

“የሀገራችንን ምህፃረ-ቃል ሳታውቂ የፈረንጁ ላይ ጉብ ብለሽ
ትንጠባረሪያለሽ አይደል?”

እሷ፦ ባክህ አሁን ወሬ ማብዛቱን ተውና “መ.ድ.ያ” ምን ማለት እንደሆነ
ንገረኝ

እሱ፦ “መ.ድ.ያ” ማለትማ ምን መሰለሽ...?

መ = መድኃኒያለም
ድ = ድፍት
ያ = ያድርግሽ

ማለት ነው” ብሏት እርፍ

መልካም አዲስ ዓመት



Share @weg_bicha