🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

【እንደመጣ፣ እንደወረደ፣ በታሰበበት ቋንቋ የተጻፈ】 Loving you, it was like ge | Scribbles

【እንደመጣ፣ እንደወረደ፣ በታሰበበት ቋንቋ የተጻፈ】

Loving you, it was like getting into an arranged marriage without knowing better.
You know, without having someone you love so the whole arrangement kind of feels...okay?

ሀገሬ፣ ከነስህተትሽ ከነጉድለትሽ የወደዱሽ አሳድገውኝ
ማንና ምን እንደሆንሽ ሳላውቅ
በልጅነቴ ላንቺ ታጨኹኝ::

Loving you, it was like imagining a person I have never seen and people talking them up for a blind date.

አንቺ የታደልሽ መሬት
ቅድስት የሚለው ገላጭ ከፊትሽ አለና
ካንቺ ሳይሆን ከሰው ከሰማሁት
በሙዚቃ፣ በፍቅርሽ ወድኩኝ፡፡
አይተውሽ እነሱ ሲያለቅሱ
ግና ባላይሽም፣ ባላውቅ ምን እንደምትመስይ
ከሚወዱሽ፣ ከሚያቀነቅኑልሸ ጋራ
አብሬ አለቀስኩኝ፡፡

Because loving you, it came from the music I grew up listening to.

እናማ፣ "ኢትዮጽያ" በተባለ ቁጥር
እነ ጥላሁን፣ እነ ቴዎድሮስ ካሳሁን ትዝ እያሉኝ
ሀገር ምን እንደሆነ ሳይገባኝ
እንዲያም ሆኖ አንቺን ወደድኩኝ፡፡

Because love was a beautiful art
and art was full of words
ካነበብኩት፣ ከገጠሙሽ አንቺን ገጠምኩኝ።
ድንገት ሲያምሽ፣ ዘመም ስትይ
"አዬ እመብርሀን ምነዉ ኢትዮጵያን ረሳሻት?''
ብዬ እንደ ሎሬቱ እኔም ተቀኘሁኝ።

Because I have been told love was blind
አይኔን ሳልገልጥ፣ ከየት እንደመጣ በማላውቀው ተስፋ አንቺን ወደድኩኝ፡፡

ሀገሬ፣ ካንቺ ጋራ ሁለት ግዜ በፍቅር ወደኩኝ፡፡
This was the first time.
ሳላውቅሽ ወደድኩሽ፡፡

And then I grew up.

ከዚያ...ቀለም መቀባትን አስለምደው
ሰንደቅሽን ባሳሉኝ መምህሮቼ
በነሱ አንቺን ወደድኩኝ፡፡
ስቀው በሚያስቁኝ በነዛ ጓደኞቼ
ሀገሬ አንቺን ፈለኩኝ፡፡
እኔነቴ፣ ማንነቴ አንቺን አልፎ ለኔ የሚደርስ መስሎ ታየኝና
ይኸው ለሁለተኛ ግዜ "ኢትዮጵያንማ እወዳታለሁ" አልኩኝ፡፡

Because love was learning you see
እናም እኔ፣ ዙሪያዬን ከከበኝ ህዝብ አንቺን ተማርኩኝ።
ሀገሬ፣ የመጀመሪያ ፍቅሬን አንቺ ላይ ሆኜ አገኘሁና አንቺን ወደድኩኝ፡፡
I felt grateful.

*In sickness and in health
Until death do us part.*


They said the best things are felt not seen
እናም ሳላይሽ ስለወደድኩሽ
በራሴ ኮራሁኝ፡፡

Tell me, is it too soon to marry someone after the second date?
Too quick to say you are in love after the first?
And perhaps, too reckless to steal blue french horn hours after meeting them?

አይኔን ጨፍኜ ያፈቀርኩሽ ሀገር፣
ተክሊል ካቆራኘን በኋላ
ያረግሽውን ካባ አውልቀሽ
አይንህን ገልጠህ እየኝ ብትይኝ
እርቅናሽ ልቤን ከከበደው
ጋብቻችን ይሰምር ይሆን?

ስትወድቂ፣ ስትቃትቺ
ከተሰማኝ፣ ከባዘንኩኝ
ለተገለጠው አይኔ
አዲሱ ፍቅር ይሄ ይሆን?

I'm not asking for a divorce yet
but perhaps we moved too fast, too soon?
If I asked for a couple more dates before the whole marriage commitment,
would it be too crude?

Would you be offended if I said, "I would like to get to know you more"?
I heard it was not the kind of thing you ask your wife for.

Would I be breaking our vows?
If i said I need space to see clearly.
Would it be degrading all I know about love?
Would it be degrading the holy matrimony?

ሀገሬ፣ loving you was like getting into an arranged marriage
but breaking up with you cause you don't fit my imagination seems a bit harsh.
So I would like to get to know you.

ማነሽ?
የነፃነት ተምሳሌት፣ የጥቁር ኩራት የተባልሽ
የፍጥረት መጀመሪያ አንቺ ድንቅነሽ
የገነት ወንዝ የሚዞርሽ
ቅድስት ኢትዮጵያ፣ ቅድስት ሀገሬ
አንቺ ማነሽ?

ስለራስሽ ብታወሪ፣ ከአድዋና ላሊበላ
ከአክሱምና ከፋሲል ግንብ
ካሸበረቀው ማንነትሽ ውስጥ
የተደበቀ ቁስልሽን ታሳያለሽ?

ሀገሬ፣ ድሮን ትተሽ ዛሬን አውሪ ብትባይ
አንገት ቀና የሚያስደርግ ታሪክ አለሽ?

ወይስ በዚያ ግዜ፣ እንትናን ድል አረኩ
እያልሽ ትናንትናን፣ ነበር ታወሺያለሽ?

ቅድስት ሀገር፣ አንቺ ማነሽ?

አይኔን ጨፍኜ፣ በፍቅርሽ የወደኩኝ
ስትወጊ የማቃስት፣ እኔስ ማነኝ?


#RANDOM_THOUGHTS