Get Mystery Box with random crypto!

ለችሮት ትግስቴ ለምወዳት ሚስቴ °°°°°°° ጀንበር ንጋት የማለዳ - የሩቅ ምስራቅ ቀጭን | የኛ🔊

ለችሮት ትግስቴ
ለምወዳት ሚስቴ

°°°°°°°
ጀንበር ንጋት የማለዳ -
የሩቅ ምስራቅ ቀጭን ጮራ፤
የደመና መውጫ ገፁ -
እንደ መላክ ምታበራ።
መልካም ሽቱ እንዳበባ -
የጣን ሞገስ የመቅደሱ፤
መልካም ቅኔ መልካም ፍቅር -
ከከንፈሯ ሚታፈሱ።
ያይኔ ብርሐን የዛ ልቤ -
የግሬ መንገድ መራመጃ:
የታቦት ደጅ የፅላቱ -
የሙክራቡ መጋረጃ-
የፍቅሬ ፍቅር መስታይቱ -
ለመውደዴ ጥግ ልኬት፤
በልቤ አለች የማትወጣ -
ከሴት ሁሉ የላቀች ሴት።