Get Mystery Box with random crypto!

አንድ እህት ያጋራችኝ እጅግ አሳዛኝ የቤተሰቧ የኩፍር ታሪክ ነው፥ በጥሞና ይነበብ አስተማሪ ነው። | AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር

አንድ እህት ያጋራችኝ እጅግ አሳዛኝ የቤተሰቧ የኩፍር ታሪክ ነው፥ በጥሞና ይነበብ አስተማሪ ነው።
══════════

አባቴ ሁለት ሚስት ነው ያለው። እኛን አልፎ አልፎ ከመዘየር ውጭ የሚኖረው ከሌላኛው ሚስቱ ጋር ነው። እኛም አልፎ አልፎ እየሄድን እንጠይቃቸዋለን። ቤታቸው ዚያራ ሄደን በምንሰበሰብበት ወቅት ታድያ ጎረቤታቸው የሆነችው የአባቴ አክስት ወሬዋ ሁሉ "እከሊት ቸርች ተፀልዮላት ተፈወሰች፣ እንትና ዳነ" ወሬዋ ሁሉ እንዲህ ነበር።

ረመዳን ላይ እንደተለመደው ለኢፍጣር ስራ ላግዛቸው ብዬ ቤታቸው ሄድኩኝ። የአባቴ ሚስት ስትበላ አገኘኋት። እንዴት በረመዳን ትበያለሽ ስልም ጠየኳት። ስላመማት እንደሆነ ነግራኝ ለአባቴ እንዳልነግረው አስጠነቀቀችኝ። እሺ ብዬ ዝም ብልም ይህ ነገር ተደጋገመ፥ ሰላት ካለመስገዷም ጋር ተያይዞ ጥርጣሬ ፈጠረብኝ።

ታድያ እህቴጋ ዚያራ ሻሸመኔ በሄድኩበት በሆነ ቀን የቤቱ ትንሿ ልጅ ደወለችልንና እያለቀሰች "አባቴን አክፍረውታል ቶሎ ድረሱ" አለችን። እጅግ ተደናገጥን፣ ተረበሽን።

ባለንበት ከተማ ወንዶ ገነት ሙስሊሙ የቀራ ባለመሆኑ በማይረባ ጥቅማ ጥቅም ተደልለው በጣም በርካታ ሙስሊሞች ይከፍራሉ። እኛ ቤት ፊትለፊት ቤተክርስቲያን ስላለ አንዳንዴ የከፈሩ ሙስሊሞች ምስክርነት ሲሰጡ ቤት ቁጭ ብለን የምናቀውን ሰዎች ድምፅ እንሰማለን። ምስክርነት ሲሰጡ ቁርዓን በጣም እንደቀሩና እስልምናና በሚገባ እንደሚያውቁት አድርገው ውሸት ሲያወሩ እየሰማን እናዝናለን።

እንደውም እኛ ካለንበት ራቅ ብሎ የሚገኝ አያቴ የምትኖርበት የላይኛው ባጃ የሚባል የገጠር መንደር ሁሉም ሙስሊም ከፍሮ አንድ አያቴ ብቻ ነው የቀረችው። እሷንም ብትሞቺ የሚቀብርሽ የለም እያሉ እንድትከፍር በእድር ያስፈራሯታል። ወንድ አያቴን ለምን እንደከፈረ ስጠይቀው ግብር ብዙ ብር መቶበት ለመክፈል ተቸግሮ እነሱ(አክፍሮት ኃይላት) እንደከፈሉለትና በዚህም ምክንያት እንደከፈረ ነግሮኛል። አባቴንም ብዙ ጊዜ ሊያከፍሩት ሞክረው አልተሳካላቸውም ነበር። የሚሰራበት የእርዳታ ድርጅትም በሀብት ደልለው ሊያከፍሩት ሞክረው ጥሎላቸው ነበር የወጣው።

የመክፈሩን ዜና እንደሰማው እያለቀስኩ ወደ አባቴ ሚስት ቤት ጉዞ ጀመርኩ። ስደርስ እናቴም ስትደርስ እኩል ተገናኘን። እናቴም ጉዳዩን ሰምታ የመስጂድ ሰዎችን ይዛቸው መጥታ ነበር። ተያይዘን የአባቴ ሚስት ቤት ገባን። አባቴ አልነበረም፥ ከሚስቱ ጋር ማውራት ጀመርን፤ የተፈጠረው ምን እንደሆነ ጠየቅናት። እሷም ምንም እንዳልተፈጠረ ነገረችን። ስልክ ደውላ የነገረችን ትንሿ ልጅ በእናትየው ክህደት ብስጭት ብላ ሮጣ ሄዳ ከአልጋው እራስጌ ስር መፅሐፍ "ቅዱስ" አውጥታ አሳየችን። በዚህ ጊዜ ጭቅጭቅ ተፈጠረ፥ የአባቴ ሚስትም እኛን ጨምሮ የመስጂድ ሰዎችን መሳደብ ጀመረች። "በኛ ህይወት ምናገባችሁ? እኛ ጌታን አግኝተናል፥" ቅብርጥሴ ምንጥሴ ማለት ጀመረች።

በዚህ መኃል አባቴ መጣ፥ ተሰብስበን ሲያየን ግራ ገባው። በሰላም እንደተሰበሰብንም ጠየቀን። የመስጂድ ሰዎች መክፈሩን እንደሰሙና እውነት እንደሆነ ጠየቁት። እራሱን ምንም እንደማያውቅ ተናግሮ ማልቀስ ጀመረ። "እውነትም እኮ ዛሬ ከነጋ ሱብሂም ዝሁርም አልሰገድኩም" አለን "ሚስቱንም ምንድነው ያደረግነው? ምንድነው የሰራነው?" እያለ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ። ሚስቱ ግን "ምንም ያጠፋነው የለም" እያለች ትቃወም ነበር። ይህን ስትል አባቴ "ተይ! አስተግፉሩላህ" በይ አላት።

ደውላ ከጠራችን ከቤቱ ትንሿ ልጅ የተፈጠረውን ሙሉ ታሪክ ሰማን። እንዲህ ነበር የሆነው፦ ጤነኛ የነበረው አባቴ በድንገት እንደማበድ ያደርገዋል። በዚህ ጊዜ ሚስቱና ጎረቤታቸው የሆነችው አክስቱ ከቤተክርስቲያን ፓስተሮችን ያመጡና ያፀልያሉ፤ ዘይት እየቀቡት "ጌታን ተቀበል" አሉት። እንደማበድ እያደረገው የነበረው አባቴም ደህና ሆኖና ከበፊቱ አህዋሉ ተቀይሮና ፍፁም ሌላ ሰው ሆኖ ጌታን ተቀብያለሁ እያለ በመዝሙር ከነሱጋ ይጨፍር ገባ።

አባቴ አቅፎን "ደርሳችሁልኛል፥ አመሠግናለሁ" እያለ አለቀሶ እኛንም አስለቅሶን ተለያየን። በሌላ ቀን ልንዘይረው ስንደውልለት ቤት እንደሌለ ነግሮን ያለበት ሄድን። ስናገኘው ግን ያለበት ሁኔታ ልክ አልነበረም። ሚስቱ ከከፈረች እንደቆየች፣ ልጆቹንም ከትንሿ በስተቀር እንዳከፈረቻቸው፣ ቤተክርስቲያንም እንደምትሄድ ሰምቶ ተጣልቶ ነው ከቤት የወጣው። እጅግ አዝኗል፥ ልቡም ተሰብሯል። "እንደከፈረች አንቺም ታውቂ ነበር?" ሲል ጠየቀኝ። እንደማትሰግድና እንደማትፆም እንደነበር እንደማውቅ ነገር ግን እዚህ ደረጃ ትደርሳለች ብዬ እንዳላሰብኩ ነገርኩት።

ሁኔታው ስላሰጋን ለመስጂድ ሰዎች ሄደን ሲህር ተደርጎበት ሊሆን ስለሚችል ሩቃኽ እንዲቀራበት ነገርናቸው። እነሱም አሁን ደህና እንደሆነና ወደ ቀልቡ እንደተመለሰ ነገሩን። በሌላኛው ቀን ልንዘይረው ያለበት ስንሄድ ግን የተፈጠረውን ማመን አቃተን። ጮኽን ተላቀስን፥ አባቴ እራሱን አጥፍቷል። እጅግ አዘንን። ከዛ ቡኃላ ግን የቤቱ ትንሿ ልጅ ከካፊር ጋር አልኖርም ብላ እኛ ቤት ይዘናት ሄድን።
══════════
ሌሎች ይማሩበት ዘንድ ሼር ይደረግ

https://t.me/Zelebet