Get Mystery Box with random crypto!

ውዱእ ሳይኖር ከሞባይል አፕሊኬሽን ቁርኣን መቅራት ይቻላልን? ~ ሞባይል፣ ታብሌትና ኮምፒዩተር ላይ | AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር

ውዱእ ሳይኖር ከሞባይል አፕሊኬሽን ቁርኣን መቅራት ይቻላልን?
~
ሞባይል፣ ታብሌትና ኮምፒዩተር ላይ የተጫኑ የቁርኣን አፖች ወይም ሶፍትዌሮች የሙስሐፍ (ሀርድ ኮፒ ቁርአን) ብይን የላቸውም።
ስለዚህ ቁርኣን ያለ ውዱእ እንዳይነካ የሚለው ሙስሐፍን የሚመለከተው ብይን በነዚህ መሳሪያዎች ላይ የሚገኘውን ቁርኣን አይመለከትም። ስለሆነም በነዚህ 'ዲቫይሶች' የሚገኘውን ቁርኣን ተጠቅሞ ውዱእ ባይኖርም መቅራት ይቻላል። የወር አበባና የወሊድ ደም ላይ ያለች ሴትም በነዚህ መሳሪያዎች ላይ የሚገኘውን ተጠቅማ ቁርኣን መቅራት ትችላለች።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor