🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ቅኔ ያለው ትውልድ

Logo of telegram channel keney_serezoch — ቅኔ ያለው ትውልድ
Logo of telegram channel keney_serezoch — ቅኔ ያለው ትውልድ
Channel address: @keney_serezoch
Categories: Literature
Language: English
Subscribers: 1.33K
Description from channel

ለነፋሳቹ ነፋስ የሚሆኑ ነገሮችን ዝሩለት . . !
ቤቴን ቤቶ ስላረጉ አመሰግናለው!
. .

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 3

2021-07-16 19:12:37 …………

" . . . የሰዎችን አእምሮ እንዴት ማርከው እንደሚ
ያሳምኑ ታውቃለክ ? አንድ ነገር መልሰው መላል
ሰው ይናገራሉ። በዚህም አገር ውስጥ የምናደርገ
ው ይህንን ነው። ነገሮችን የራስ ማድረግ ጥሩ
ነው ፣ ተጨማሪ ገንዘብ ጥሩ ነው ፣ ተጨማሪ ንብ
ረት ጥሩ ነው ፣ ተጨማሪ ንግድ ጥሩ ነው ፣
ተጨማሪ ጥሩ ነው . . . እኛም እንደጋግመዋለን
ያንኑ ይደጋግሙልናል - ማንም ሰው ለትንሽ ጊዜ
እንኳን ቆም ብሎ ሌላ ለማሰብ እስከሚቸገር
ድረስ ደጋግመው ይነግሩታል። መካከለኛ ኑር
ያለው ሰው በዚህ ሁሉ ጭጋግ ስለተሸፈነ ጠቃሚ
ለሆኑ ነገሮች ምንም አይነት አስተሳሰብ የለውም

በህይወቴ ከሄድኩባቸው ቦታዎች ሁሉ ሰዎች
አዳዲስ ነገሮችን ለማግኘት ሲሮጡ አጋጥሞኛል
አዲስ መኪና ለመያዝ ፣ አዲስ ንብረት ለመያዝ ፣
የሚገርምህ ደሞ ስለቃዎቹ ሊነግሩህ ይፈልጋሉ
'ምን እዳገኘው ገምት? ምን እዳገኘው ታውቃለህ
?' ይሉሃል።

ይህን ሁልግዜ እንዴት እንምተረጉመው ታውቃለ
ህ ? እነዚህ ሰዎች በፍቅር የተራቡ ስለነበሩ ምትኩ
ን ይቀበላሉ። አለማዊ ነገር አቅፈው በመሰብሰብ
በምላሹ ምቾትን ይጠብቃሉ። ነገር ግን ፈፅሞ
አልሰራም። አለማዊ ነገሮች ፍቅርን ወይም ጨዋነ
ትን ወይም ርህራሄን ወይም ወዳጅነትን ስሜት
ሊተኩ አይችሉም።

ገንዘብ ርህራሄን አይተካም። ስልጣንም ለርህራሂ
ምትክ አይሆንም።ምንም ያህል ገንዘብ ወይም ስ
ልጣን ቢኖርህ እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገር
በምትፈልግበት ጊዜ ያንን ስሜትህን እስከምትፈ
ልገው ድረስ ሊያረካህ እንደማይችል አሁን እዚህ
ተቀምጪ በሞት አፋፋፍ ላይ እያለው ልነግርህ
እችላለው። . . . "

{ማክሰኞን ከሞሪ ጋር - ከገፅ 94 -95 የተወሰደ
ትርጉም *ባህሩ ዘርጋው ግዛው}


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
92 views16:12
Open / Comment
2021-07-16 07:47:14 ~~~~ ኦስካር ዋይልድ~~~~



ትውልድ- አየርላንዱ ደራሲ ኦስካር ዋይልድ ፣ እ.
ኤ.አ ጥቅሞት 16 ቀን 1854 በአየር ላንድ ዱብ
ሊን የተወለደ ሲሆን በትምህርቱ " ሰቃይ " ተማሪ
እንደነበር በዩንቨርስቲ ቆይታው ክላሲካል ስራዎች
ን በጥልቀት ማጥናት የህይወት ታሪኩ ይጠቁማ
በዘመናዊ የእንግሊዞች ድራማ በተለይም በኮሜ
ዲ ዘውግ አንቱ ከሚባሉ ፀሀፌ ተውኔቶች አንዱ
ነበር። ዋይልድ ከዚህም ባሻገር ገጣሚና ኃያሲ
ሲሆን ጋዜጠኝነቱም ሳይጠቀስ የሚታለፍ አይደ
ለም።

The Happy prince እና A House of Pome
granates and others (1888) የተሰኙት ሁለ
ት መድብሎች በህፃናት መፅሐፍት ዘርፍ ቢመደቡ
ም በህፃናትም በአዋቂዎችም ዘንድ እኩል ተነባቢ
ሊሆኑ በቅተዋል። The picture Of Dorian Gr
ay (1891) የተሰኘው ብቸኛው ረዥም ልብወለ
ዱ ፣ በሥነፅሑፍ ሕይወቱ ጉልህ ቦታ የያዘ ነው።
ኦስካር ዋየልድ በበርካታ ቲያትሮችም ይታወቃል።
Lady Windermere's Fan (1892) ፣ A Wo
man of no Importance (1893) እና The
Importance of being Eamest (1895) አ
ብይት ሥራዎች ሲሆኑ የመጀመሪያው ወደ አማር
ኛ ተተርጉሞ ፣ በሀገር ፍቅር ተመድርኳል።በመ
ጨረሻም ያሳተመው The Balled Of Reading
Goal (1898) የግጥም መድብሉም ተጠቃሽ
ስራ ነው።

የእንግሊዝ ጠ/ሚ የነበሩት ዊንስተን ቸርችል፣በ
አንድ ወቅት ፣ ከሞት በኋላ በሰማይ ቤት ማንን
አግኝተው ማነጋገር እንደሚሹ ተጠይቀው ሲመል
ሱ ፣ ቅንጣት ሳያቅማሙ ፣ "ኦስካር ዋይልድ!"ማለ
ታቸው ይነገራል። ~~~~~

ውድ ቤተሰቦቼ እውነት እላችዋለው ሰውየው
ምዕታት ነው፣ እጆቹ ቃላትን በዕንቁ መልክ ነው
ወረቀት ላይ ሚያሰፍራቸው . . . . . . . . .

…………… አንብቡለት. ግብዣዬ ነው .


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
66 views04:47
Open / Comment
2021-07-15 10:14:34 “listen to the reed -flute
How it complains
Telling the tale of separation
Ever since i was cut from the reed bed
Men and Women have moaned in my lament
I seek out a heart that, being separated
Is Shred into pieces
Then i can describe the pain of longing
Whoever has gone from his origin
Seeks to return to the days of his union. (ሩሚ )

“የዋሽንቱን እሮሮ ስሙ፤
” ከመሬት ከተገነጠልኩ ጀምሮ እንዲሁ አዜማለው ፤ የሰው ልጅም ከኔው ጋር አብሮ በሀዘን ይተክዛል። ከወደደው ነገር የተለየ ልብን እፈልጋለው በዜማዬ እጠራለው፤ እንዲህ አይነት ልብ ሳገኝ፤ በእንጉርጉሮዬ የናፍቆትንና የመጠበቅን ህመም አስረዳዋለው። ከምንጩ የራቀ ማንኛውም ነፍስ፤ ወደ ምንጩ ለመመለስ ይናፍቃል” ” እንደማለት ነው።

እንደናፈቀ ሰው ስለናፍቆት አሳምሮ የሚጽፍ ማን አለ? ወዶ እንደተለየ ሰው ስለፍቅር ከልቡ የሚያዜም ማን አለ? ስለፍቅር የሚሰብኩት፤ ወደፍቅር ለመመልስ የሚናፍቁት ናቸው። ስለእውነት የሚለፍፉት፤ ወደ እውነት ለመመልስ የሚመኙ ነፍሶች ናቸው። ልክ መቃው ወደመሬት ለለመለስ ካለው ናፍቆት የተነሳ እንደሚያንጎራጉረው ሁሉ።

እንግዲህ የጠቢባን ሁሉ ጩኸት፤ ከሚናፍቁት እውነታ ጋር ለመገናኘት ቢሆንስ? ጸሀፊያን፤ ደራሲያን፤ ሰዓሊያን፤ በምንጩ እና በእኛ መካከል ያለውን ክፍተት ቢሆንስ ጥበብ ብለው የሚሰጡን? የዋሽንት ዜማ የሚያስተክዘን ምናልባት የምንሸሽገውን ክፍተት ስለሚያስታውሰን ይሆን? መቃው ወደ መሬት ለመመለስ ናፍቆ እንደሚጮኸው ሁሉ፤ የእኛ ወደምንለው እውነት ለመመለስ ያለን መናፈቅ ቢሆንስ በተለያየ መልኩ የሚያስጮኸን?
ይህ ክፍተት ሀዘን ቢመስልም ውበት ግን ያለው ይመስላል………ደስ የሚል ዜማ

{ኬት እዳገኘሁት አላስታውስም }


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
111 views07:14
Open / Comment
2021-07-15 10:13:52
108 views07:13
Open / Comment
2021-07-14 20:33:00
በእውነቱ እውነተኛ ዕውቀት ለማግኘት የሚፈልግ ሁሉ በከፍታው ላይ ያለውን ኮረብታ መውጣት አለበት ፣እና ወደ መድረኩ የሚወስድ ምንም አይነት የንጉሥ መንገድ ስለሌለ እኔ በራሴ መንገዴን ዚግዛግ ማድረግ ነበረብኝ፡፡ወደኋላ ደጋግሜ ተንሸራትቻለው ፣ እወድቂያለሁኝ ፣ እንደገና ለመቆም እጣጣራለው፣ ከተሰወሩት መሰናክሎችን ዳር ዳር እሮጣለሁ ፣ ቁጣዬን አጣሁ እና እንደገና አገኘሁ እና በተሻለ ሁኔታ እና ቦታ አስቀመጥኩት፣ ወደፊት ቀጠልኩኝ ፣ ጥቂት ተስፋ አገኘሁ፣ እንደተበረታታሁ ይሰማኛል ፣ የበለጠ በጉጉት ትነሳውኝ እና ወደ ላይ ከፍ አልኩኝና እና ሰፊውን አድማስ ማየት ጀመርኩ፡፡እያንዳንዱ ትግል ድል ነው ፡፡ አንድ ተጨማሪ ጥረት እና ፍላጎት እኔን ወደ አብረቅራቂው ደመና ፣ የሰማያዊው ሰማይ ጥልቀት እና የፍላጎት ኮረብታዎችን ደረስኩ ........................

ሄለን ኬለር ( The story of my life)

╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
919 views17:33
Open / Comment
2021-07-13 10:32:35

አብዛኞቻችን ሕይወታችንን የምንመራው ነገን በመፍራት ነው፡፡ በተለይም በማይመች አካባቢ ስንኖር ሕይወታችን እንዲሁ የሚያልቅ ስለሚመስለን ሐዘናችን ይጨምራል፡፡ ሕይወት ትጨልምብናለች፡፡ የሕይወት ጥያቄዎችም መነሣት የሚጀምሩት በዚህ ጊዜ ነው፡፡ አሁን ለመሥራት እስከተነሣን ድረስ በሕይወታችን ረፈደ የሚባል ጊዜ ባይኖርም፣ የሰው ልጅ ግን ከሕይወት ይልቅ ለሞት፣ ከደስታ ይልቅ ለሐዘን፣ ከመቀጠል ይልቅ ለማቆም የቀረበ ፍጡር ነው፡፡ ለዚህ ነው በሕይወት ዘመኑ ሲለፋ፣ ሲዳክርና ሲባዝን የሚታየው፡፡

በሕይወት ከመኖር ይልቅ መሞት ይቀላል፡፡ ለመኖር፣ መሥራትና መጣር፣ መውጣትና መውረድ ሲያስፈልግ፣ ለመሞት ግን ምንም ሳይሠሩ ቊጭ ማለት በቂ ነው፡፡ ምክንያቱም ከአፈር የተሠራው ሥጋ ለመኖር አፈር ይፈልጋልና፡፡ እኛ ሰዎች አሳባችን ከምንኖርበት ዓለም የሰፋና የጠለቀ ቢኾንም፣ እኛ ግን ይህንን ዘንግተን በተቈጠረው የሕይወት ዘመናችን ከሰፊው ራሳችን ይልቅ ወደ ጠባቡ ውጪ በመመልከት በሙሉ ማንነታችን ባዶነትን የምንላበስ፣ በክቡር ሥጋችን ውርደትን የምንከናነብ፣ በምክንያት በመጣንባት ምድር በዋዛ ኖረን በዋዛ የምናልፍ ነን፡፡


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
205 views07:32
Open / Comment
2021-07-10 06:30:07 ……………

"በጥሩ ሁኔታ የታጥቅህ ቢሆን እንኳ በከፍተኛ ስሜት በመነሳት ባዶ እጅህን(ሣትታጠቅ) መገኘት እውነትኛ ሰላምን ያስገኝልሃል:: ከጥላቻና ከፍርሃት ሞት የተሻለ ነው ራስንም የተጠላና የተፈራ አድርጎ ከመኖር ይልቅ ሁለት ጊዜ ሞት ይሻላል " ይላል ኒቼ

እንደ ኒቼ ግንዛቤ ሰው ሰቆቃ የተሞላበት ጥያቄ ማንሳቱ ተገቢ አይደለም :: ለምን እኔ እንዲህ ሆንሁኝ? የሚል ጥያቄ ትክክል አይደለም:: እንደዚህ አይነት ማጉረምረምና ማዘን ተፈጥሮን - የምንኖርባትን ዓለም - ነባራዊ ሁኔታ በትክክል ከአለመረዳት የሚመጣ ስሜት ነው :: ዓለም ምስቅልቅል ናት ህይወትም በችግር የተሞላች ከንቱ ነገር ናት:: ይኼን ሁኔታ አለመረዳት ለምን እንዲህ ሆንኩኝ?- ለምን ይህ ይሆናል? እንላለን:: ትክክለኛ የሚሆነው ግን እጃችንን ዘርግተን ችግሮችን ሁሉ እንደአመጣጣቸው መቀበል ነው:: ይኼን በማድረጋችን ተሸናፊዎች ሣንሆን ራሳችንን ጠንካሮች እናደርጋለን ::

ለኒቼ ህይወት በመከራ የተሞላች ናት:: መከራንና ህይወትን ነጣጥለን ማየት አንችልም :: ህይወት እስካለ ድረስ ስቃይ አለ:: በሌላ አገላለፅ ህይወት ማለት ሥቃይ ያለበት ኑሮ መኖር መቻል ነው:: ህይወትንየምንወድ ከሆነ እስከንፍጧ -እስከዝባዝንኬዋ- በህይወት ውስጥ ያለውን መከራ አምኖና ተቀብሎ መኖር ነው:: በሌላ አነጋገር ችግር አይኑር ማለት ህይወት አይኑር ማለት ነው ይህ ደሞ ህይወትን መቃወም ነው :: ይህ ደግሞ ስህተት ነው ስለዚህ ስንኖር መከራን ሞትን ጭምር በፀጋ መቀበል አለብን:: ሞት አንድ ችግር ነው ነገር ግን የህይወት ገፅታ ነው :: የሞትን ችግርነት ለማሳየት ኒቼ እንዲህ ይላል "የማይገድለኝ ሁሉ ጠንካራ ያደርገኛል"

በዚህ መሰረት ለኒቼ ሞትን ለማምለጥ ሞትን ለማዘግየትና ከስቃይ ለመዳን የሚደረጉ ባህላዊ ሃይማኖታዊ ወይም ሳይንሳዊ ነገሮች በሙሉ የህይወት ነባራዊና ተፈጥሮዊ መገለጫ የሆኑትን ሥቃይና ሞትን የሚቃረን በመሆኑ ሰውን ደካማና ፈሪ ከማድረግ ውጪ የሚያስገኘው ነገር የለም ለኒቼ ከኖሩ ላይቀር መከራንም ሞትንም ሣይፈሩ መኖር ነው!!
{በፍልስፍና መደመም ገፅ _47]


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
41 views03:30
Open / Comment
2021-07-08 07:31:29 ……………

ሰው ሦስት ጊዜ ይሞታል ይላሉ፡፡ አንድ ሲወለድ ሁለት ወደመቃብር ሲወርድ ሦስት ከሞተ በኋላ ሲረሳ፡፡ አንዳንዶች ከሞቱ ከረዥም ጊዜ በኋላ ይረሳሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ በሕይወት እያሉ የተረሱ አሉ፡፡ከምዱሩ በላይ የሚንቀሳቀሱ
ሙታን እና ከምድሩ በታች የተኙ ሙታን ብለን
ለሁለት ከፍለን ለየብቻ ብንበትናቸው ኗሪው
ሟች ይበዛ ነበር !!

ብዙ አይነት ሞት ሳይኖር አይቀረም፡፡ በሕይወት መኖር ብቻ ሙት ላለመሆን ማረጋገጫ ሊሆን አይችልም፡፡ እስትፋስ ያለው ሙታን በየቦታው አይጠፋምና፡፡ አንድ ሙታን ጓደኛ በአንድ ወቅት ነበረኝ፡፡ በቁሙ ለራሱ የሙሾ ግጥም የሚጽፍ፡፡ የሱን የትንሳኤ ብስራት ለመስማት ጆሮዎቼ ምንም ያህል ቢቀሰሩ ድምጹ ከጣፋብኝ ቆየ፡፡

ኮንፊውሸስ ስለሕይወትን መረዳት ያልቻልክ እንዴት ስለሞት ታስባለህ ይላል፡፡ ሕይወት ግራ ሲገባን፣ ትርጉሙ ሲወሳሰብብን ታዲያ ስለሞት ብናስብና ብንመራመር ምን ችግር አለው፡፡ ኮንፊውሸስስ ምን ቆርጦት ነው ይህን አስብ፣ ይህን አታስብ እያለ የሀሳብ ገደብ ሊጥልብን የሚቃጣው፡፡



እጄ ላይ የብር ላስቲክ አድርጌአለሁ፡፡ ከማደንቀው አስተማሪዬ የኮረጅኩት ቄንጥ/style ነው፡፡ ላስቲኩን እያየሁ ሕይወት እንደዚህ ላስቲክ ናት አልኩኝ፡፡ በየትኛውም አጋጣሚ ልትበጠስና ልትጣል ትችላለች. . . ! ታድያ ለሚጣለው ስጋችን ይሄ ሁሉ የጥላቻ አምልኮ የት ያደር
ሰናል ? ምን ያህልስ ያሻግረናል?



╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
166 views04:31
Open / Comment
2021-07-04 12:17:23
ውበት እንደርሶ ነው ፣ የሃገር ዛፍ ፣ ያሃገር ካስማ
እውነት ፍቅር የደግነት ሚዛን . . . ሞት እኮ አይቀርም የትም አለ አዝለን አቅፈን የምንዞረው ስንቃችን ነው ፣ ሞት ካልቀረ ግን መሞት እንደርሶ ነው !!

………… መውለድ ያላቆመ ፣ ያልነጠፈ ጡት ፣ ያልዛለ ትከሻ ፣ ያልደከመ ጀርባ የት አለ እናትነት
ወልዶ ማቆም ያልታየበት ? ወጣትነት ሳይል እርጅና ለሃገር የተከፈለ መስዋትነት!

ምን ይወራሎታል ስለእርሶ ? ቃላት በራሱ እኮ ያፍራል ደግነቶን አሳንሳለው ብሎ!!

መሞትስ እንደርሶ ነው ፣ ሞቶ መኖርን መምረጥ !!

እረፉልን እናታችን !! እረፉልን



@keney_serezoch
49 viewsedited  09:17
Open / Comment
2021-07-02 20:41:13
……… ድንኳን ………

አንዱ ቤት ዑዑታ -- አንዱ ቤት እልልታ---
እንዴት ነው አገሩ-- ?
ምንድነው ነገሩ--- ?
አንዱ ደረት ጥሎ---- ሙሾ ሲደረድር--
አንዱ አደጌር ጥሎ --- አጨብጭቦ ሲድር
በዚህ ድንኳን ሸኘን ---
በዚያም ድንኳን ሸኘን ---
ለወሬ ነጋሪ --- የሰው ያለህ ሲባል ---
አለን እኛ ብቻ ---
አለን አለን አለን
ሁለት ቤት ተገኘን !
በኢዝም በወዝም ----
እንዲያው ዝም እንዲያው ዝም !
ዑዑታው እልልታው ---
ቀልጧል በየቦታው !!
{ሙሉጌታ ተስፋዬ}


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
1.2K views17:41
Open / Comment