🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ቅኔ ያለው ትውልድ

Logo of telegram channel keney_serezoch — ቅኔ ያለው ትውልድ
Logo of telegram channel keney_serezoch — ቅኔ ያለው ትውልድ
Channel address: @keney_serezoch
Categories: Literature
Language: English
Subscribers: 1.33K
Description from channel

ለነፋሳቹ ነፋስ የሚሆኑ ነገሮችን ዝሩለት . . !
ቤቴን ቤቶ ስላረጉ አመሰግናለው!
. .

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 11

2021-05-15 11:29:29
ተስፋ በርግጥ የወደቀውን ያነሳል፤ የተሰበረውን ይጠግናል።
ስለዚህ ዛሬን በደስታ እየኖርህ ነገ የተሻለ ቦታ መድረስ እንደምትችል በፈጣሪ መልካም ተስፋ አድርግ። ኹኔታዎች ምቹ ባይመስሉም ተስፋህን ግን አታርቀው፤ ሁሌ ለችግርህና ለሐዘንህ ተስፋን አሳያቸው። ሕይወትህ መከራ፣ ችግር፣ ሐዘን ውስጥ ቢገባም በቅርብ ወደ በለጠ ደስታ፣ ድልና ስኬት እንደምትሸጋገር እመን። በምታልፍበት የሕይወት ችግር ውስጥ የምትኖረው ለጥቅት ጊዜ ብቻ እንደኾነ ለችግርህ ንገረው። በነገ መልካም ተስፋ ዛሬን በደንብ ጠንክረህ ሥራ በደስታም ኑር።

ሜሎሪና

╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
185 views08:29
Open / Comment
2021-05-14 19:05:39 <<…የምድር ስፋት ሞታችንን ኢምንት አድርጎታል። ማልዶ የሚሰማው መርዶ ዱብ ዕዳነቱ ለሟች ቤተሰብ ብቻ ነው። ሟች በሄደ ጊዜ...ሕይወት በሚወዱት ሰዎች ዘንድ ትቀዘቅዛለች። በቀሪው ዓለም ግግር በረዶ የሚያቀልጥ ነዲድ ፀሐይ እጁን ይዘረጋል። ሕይወት ሞቆ ይቀጥላል። የማናውቀው ሰው ሞት አያስገርመንም። አይከብደንም። ብዙ ሰዎች በከባድ ሕመም ውስጥ እንዳለፉ የምንረዳው ሞት ቅጥራችንን አልፎ ቤተሰባችንን፥ የእኛ የምንለውን ሰው በጎበኘ ጊዜ ነው። ያኔ....የማጽናናት ቃል ለልብ ጠብ እንደማይል እንታዘባለን።

ጊዜና ትዝታ ነን። ቆዳችን ስባችንን ብቻ ሳይሆን የኖርነውን ጊዜ ትዝታ ጭምር ነው የጋረደው። በዓይን ስንታይ አሁንን ነን። ነገር ግን ዓመታትን በልተናል። በደማችን ውስጥ የሚርመሰመሰው ዥንጉርጉር ትዝታ ነው። ያለፈውን ጊዜ፣ ያለፈውን ስሕተት ወደ ኋላ መልሶ የሚያስተራርም አዳኝ ልዕለ ሰብእ የለንም። ሆኖም ሰዎች ነን። በዚህ ምድር ላይ ሰው ሆነን ስንኖር ይህ የመጀመርያችን ነው? አናውቅም። ትውስታው የለንም። ወደ ኋላ መመለስ ቢቻል ብለን እናልማለን። ሕልሞቻችን በሕዋው ላይ ይተምማሉ። ተስፋዎቻችንም በሰማያት ላይ ይዳምናሉ። ስለፍቅር ብዙ መሥዋዕትነት ከፍለናል። ስለሰላምም ጦርነት ዘምተናል። አሁን ድረስ ልክነቱን አናውቅም። ቢያልፍም ጮክ ብለን የምንናገረው ጸጸት የለንም። ስለሞቱት ስንል፥ ስለከፈልንውም መሥዋዕትነት ስንል ዝም ማለትን እንመርጣለን። ...>>

" ትዝታሽን ፡ ለእኔ ትዝታዬ ፡ ለአንቺ...ገጽ 47-48


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
100 views16:05
Open / Comment
2021-05-14 19:05:33
97 views16:05
Open / Comment
2021-05-12 18:21:06
……ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዬች በሙሉ እንኳን ለታላቁ የረመዳን ኢድ አል ፈጥር አደረሳቹ!!!!

…… ጥፍጥ ያለ በዓል ይሁንላቹ!!


"የአላህ ባርያ ወንድሙን በመርዳት
ላይ እስካለ ድረስ አላህም እርሱን
ይረዳዋል።" (ሰ.ዐ.ወ). . ይህን ጣፋጭ ቃል በማስታወስ ያለው የሌለውን ወንድሙን በማስደሰት ቀኑን ሽብርቅ ብላቹ ዋሉበት!!


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
134 views15:21
Open / Comment
2021-05-12 15:25:46 ጋዜጠኛ፦ ለአንድ ሳምንት ዘሚ ስልኳን አጠፋፍታ ጥፍት ብትል በጉዳዩ ላይ ያገባኛል የሚልና የሚከራከር ሰው አለ ይሆን ?


ዘሚ ፦ "አለ ብዬ አስባለሁ ፣ ይኖራል ። ይሄን ያህል የሚጮኹ ባይሆንም። አሁንኮ ስብሰባ ላይ ሌላ ነገር ልናገር እጄን ሳነሳ ኦቲዝም ልትል ነው ሲሉ ሰምቻለው ፤ ኦቲዝሟ ሴትዮ ይሉኛል። "አየሃት ያቺ ሴትዮ አወቅካት ?" ሲባል ፤ ኦቲዝሟ የሚሉም አሉ።

እኔ ባልኖር የሚናገር የለም ሳይሆን የሚያሳዝነኝ የሰዎች ተስፋ አጠፋለሁ ብዬ አዝናለሁ። መኖር የምፈልገው አንድም ለልጄ ነው ፤ በዛም ላይ ለእነዚህ ልጆችና እናቶች ነው። ምክንያቱም ፊቴ እንኳን ትንሽ ከተከፋ እንዴች እንደሚደነግጡ። ተስፋቸው ሆኜ ስለሚያዩኝ ይደነግጣሉ ፣ ይፈራሉ። አንዴ ታምሜ ነበር ያኔ እንዴች እደሆነ መናገር ይቸግራል። ተስፋቸውን አጨልምባቸው ይሆን ብዬ እሰጋለሁ። ፈጣሪንም አትውሰደኝ እስኪስተካከል ፤ ይህን ቤት እስክሠራ ድረስ እለዋለው።". . . . በአንድ ወቅት ከሰጠችው ቃለ መጠይቅ ውስጥ የወሰድኳት ነው . .


# አትውሰደኝ አለችው ፣ ወሰዳት . . ምን አልባት ጭወቷን እንድንሰማው ይሆናል . . . ምን መፃፍ እዳለብኝ አላውቅም እኔ እራሴ. .……ለብላቢ ሃዘን ነው !! ዋርካው ተነስቶ ጠራራ ፀሃይ ሲያቃጥል ተሰምቶኛል…… ብቻዋን አልሄደችም ፣ ብዙ ሸፋኝ የብዙ እናት ነች. . . ልል ምፈልገው . . አንድ ብርም ቢሆን እንኳን ያለን ይሄ ማዕከል እንዲሰራ የበኩላችንን እናርግ ነው. . . ስለነበረች ያልቃል ብዬ እርግጠኛ ነበርኩ ሚጎድል አይመስለኝም ነበር . . አሁን ግን …………

…………እና ያለንን እንስጥ . . .. . ለመስጠት ሚሊየን ማገላበጥ አይጠበቅም መመረጥ ብቻ ነው ሚያስፈልገው . . . የተመረጥን እንሁን !!!


በብዙዋን ነፍስ ውስጥ ትኖርያለች የኔ ልባም ሴት ፣ ከቀይ እንቁ በላይ የሆንሽው ዘሚዬ !!



@keney_serezoch
135 views12:25
Open / Comment
2021-05-11 14:45:36
. . አንዳንድ ሰዎች አሉ . . በጨለማ ተጉዘው ለሌላው ብርሃን የሚሆኑ አንቺ ያቺ ባለነፍሳም ብርሃን ነሽ. . ሁሌም ትሆኚያለሽ . . !!


መልካምነት ታላቅ ውብ እናቷን አጣች !!


ዘሚ የኑስ- እናት ፣ እህት ፣ የሴት ውሃ ልክ
. . . የመብቃት ጥግ . . . የማጠፊ እውነት!



ለምንሽሽ ሁሉ መፅናናት እመኛለው!!



@keney_serezoch
116 viewsedited  11:45
Open / Comment
2021-05-09 10:45:26
ቀን / 01 9 2013 እሁድ

የሳምንቱ የቻናሉ ተንቀሳቃሽ ምስል ……………


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
70 views07:45
Open / Comment
2021-05-09 05:50:32
ቀን / 1 9 2013 እሁድ

የሳምንቱ የቻናሉ ምስል ……………


•••••• ይናገራል ሚስጥር••••••


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
103 views02:50
Open / Comment
2021-05-08 05:51:14 ………

«እየው እጄ ሞቶ፤ እየው እግሬ ሞቶ
ያስለፈልፈኛል ሆዴ ብቻ ቀርቶ»

ሺህ ሰዎች ተሳስተው አንዱ ብቻ ልክ ሊሆን ይችላል ... አዎን መቶ አህዮች ባንድነት ሲያናፉ ከአንድ መሲንቆ የተሻለ ጣዕም ሊኖራቸው አይችልም። አሁንም ቢሆን እኔ የማምነው ከብዙ ምላስ በትንሽ ስራ ነው።

ኢትዮጵያ እጆቿን ወደሰማይ ዘርግታ ፀሎት ስታደርስ በቀለም ትምህርት ናላው ሰክሮ በእጁ መስራት ከማይፈልግ ትውልድ አድነኝ ሰውረኝ ብላ መለመን አለባት።

አእምሮ ያሰበውን ያንን ስራ ላይ እጅ ማዋል አለበት። በእጅ አማካይነት በስራ ያልተገለጠ ሃሳብ የማይታይ፤ የጋን መብራት ሆኖ ይቀራል። እርግጥ ዓለም በሃሳብ ባህር የሚዋኙ መለኮት የሚታያቸው ሰዎች ያስፈልጓታል። ያለእነርሱ ወደፊት ልትራመድ አትችልም። ይሁን እንጂ የአክሱም ሀውልቶችና የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት የታነፁት በህልም ብቻ አይደለም። በእጅ ነው። የፖለቲካ ፍልስፍናን በመለፈፍ ብቻ ኢትዮጵያን እናሻሽላለን ማለት ዘበት ነው። የመንፈስ ደካማነት ምልክት ሊሆን ይችላል። ምላስን ከማወናጨፍ ይልቅ እጅን ለትንሽ ስራ መዘርጋት የበለጠ ወኔን፤ ቆራጥነትንና መስዋእትነትን ይጠይቃል።

አእምሮን የሚመራው እጅ ነው ማለቴ አይደለም። እጅ ለስራ እንዲቃጣ የማያደርግ አእምሮ ህሊና ቢስ ነው።

እምነትና ድርጊት ከተለያዩ ምሠሶው በምስጥ እንደተበላ ቤት መዛግ ከዚያም መፍረስ ይመጣል - ወና ቤት መሆን።

{የህሊና ደወል _ ከበዓሉ ግርማ}


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!
66 views02:51
Open / Comment
2021-05-06 15:06:57 ……………

"ከዛጎሌ ውስጥ መውጣት ብቻ አደለም ምፈልገው. . . ዘጎል ውስጥ ሆኜም እደነበር መርሳት ጭምርም እንጂ " አለችኝ. .

ቆንጆ ሳይሆን ቆንጅና እራሷ ናት . . ተሰብራ እራሱ ሙሉ ምትሆን ሴት ናት ………

"የማልችለውን ተሸክምያለው እያልኩክ አደለም ፣ ምችለው ከብዶኛል እንጂ……… አሁን ህመም አለው . . ጠባሳውን እየው . . ፀጉሬን ተመልከት
፣ ተንጨባሮዋል አደል? ፣ እግሮቼን እያቸው እዴት እዳደፉ ፣ የጥፍሬን ቆሻሻዎች ተመልከት ፣ የሰውነቴን ጠረን ምን እደሚል አፍንጫክን ጠይቅ. . . ስለማይታየው የውስጤ ህመም ምስክር ናቸው………… " ብሷቷ ንግግሯን ገታው………

ፀጉሯን ፣ እግሯን ፣ ጥፍሯን ቀስ በቀስ ከዚህ በፊት እደማያቃቸው ሰው አየዋቸው . . . . . ምንም ሆና ውበት ናት !

"አልጋዬ የእሾህ አልጋ ፣ ምመገበው ምግብ የሰው የሰው ስጋ ፣ የምጠጣው ውሃ ደም ደም ይመስሎኛል. . . ለምን መሰለክ ? ውስጤ በቀልን የተጠማ ስለሆነ ነው"

በሃሳባዊ ሃዘኔ ውስጥ ይችን ውብ የማር አበባ ስለቀጠፈው ንፋስ አስባለው . . . ከዚህ በኃላ ቅዝቃዜን ጠልታ ስለምትሰቃይባቸው ሞቃት ወቅቶች ተክዛለው……

"ስለፈሰሰው ደሜ ደም ፈልጋለው ስለተንገላታው ስጋዬ ስጋ እሻለው . . በስለት ስለተቆራረጠው ነፍሴ ነፍስ ከጅላለው. . ይሄን ሚመልስልኝ አለ ? "

ውስጧ ሲወራጭ ይሰማኛል . . እደታረደች ወፍ ትፈራገጣለች. . . ያለችውን ምጠይቅበት ደረጃ እዳደርስ ባረግ ብዬ እመኛለው. . ግን ምኞት ነው. . . ለዛሬ ማዳኛ መድሐኒት ኬት ላምጣ ?

"ከመውደቁ በፊት ከፍ ከፍ ያለ የሰው ልብ ነው
ያረደኝ . . .ሳይከብር የተዋረደ . . አሁን እኔ የነጠፈ ደረቅ የውሃ ጉድጓድ ሆኛለው . . መጦኛላ!

ገና ምንጭ ናት እኮ . . . . በውብ ለምለም ቄጤማዎች መሃል የተደበቀች ጣፋጭ ምንጭ፣
እዲህ ብዬ ልነግራት ፈልጋለው ግን ደሞ ፈራለው. . !

"በፍርድ ጊዜ እውነትን አራቁብኝ ፣ ገልገበው እርቃኔን አስቀሩኝ ፣ አእምሮዋቸው ጎሎዋልና እንዴት ልቻላቸው ? ለቀሚሴ መቀደድ ለሷ መጨቅየት . . ተገላቢዋ እኔ እያለው ለገላቢው ወግነው ቆሙ . . . ለነዚህ ፍጡር እጄ ስለት
ብታነሳ ምኑ ጋር ነው ሃጥያቴ ?"

አሳዘነችኝ ፣በበቀልና በምህረት መሃል ያለችን ነፍስ እደማየት ያለ ህመም ይኖር ይሁን . . . ?

ቀስ ብዬ ተጠጋዋት ፣ ሸሸችኝ . . ጠተጋዋት ሸሸችኝ . . .

"እፈራችዋለው ፣ የአይኖቼ ብሌን ስለእናንተ ጨለማን ያያል . . እራሴን ለቦዘኔነት ሳልሰጥ
ነው የተዋረድኩት. . ምድረ በዳ ሆኛለው !"

አይኖቿ እንደ ርግቦች ናቸው . . ያለችው ጨለማ የለም ፣ሮማንና የጣፈጠ ፍሬ ፣ከሽቱ ሳር ጋር ያለባት የገነት መንገድ ናት! በሱፍ አበባ መሃል እደሚሰማሩ እንደሚዳንቆ ግልገሎች ገና ብቅ ብቅ ያሉ የልጅነት ሃሎች አሏት . . እንዴት ብዬ ስትነድ አያታለው ?

አሁን ላቅፍት አላሰብኩም ከዚህ በኃላ መች እደማስብም አላውቅም ግን አብርያት ታምሜ አብርያት ልድን ወስኛለው!

{#ት ዝ ታ }

@tizetawe
@tizetawe
@tizetawe
175 viewsedited  12:06
Open / Comment