2021-05-31 12:46:51
…………………
መፅሃፉ The Count of Monte Cristo ይሰኛል።
ፈረንሳይ ውስጥ በነበረው የፓለቲካ ሽግግር ሳቢያ ሁነቱ ሰለባ ስላደረገው ወጣት መርከበኛ ይተርካል።
ወቅቱ ናፖሊዮ እና ሊዊ 16 ኛ ያልረገበ ውጊያ የሚያካሂዱበትና መንበር ለመለዋወጥ የተፋለሙበት ጊዜ ነበር።
ይህን ደራሲው ለመፅሃፉ እንደ መቼት የተጠቀመው ሲሆን እልፍ ገፀባህሪያትን በመመስረት ታሪኩን ውብ አርጓ ይጓዛል።
አብዛኞች ድርሰቶች ታሪክ የሚነግሩበት የሴራ አወቃቀር ቀጣዮቹን ዋና ክፍሎች ይዞ የሚከወን ሲሆን
የታሪክና ገፀባህሪ ትውውቅ (exposition)
ግጭት (conflict)
ጡዘት/ልቀት (climax) ከደረሰ በኋላ
የሁነት መርገብ (Falling Action)
የትልም ማሳረጊያ (resolution ) ላይ በመድረስ ይጠናቅቃሉ።
ይህን መፅሃፍ ልዩ የሚያደርገው የትልም / ሴራ (plot) አመሰራረቱ እንደማንኛው መፅሃፍት ከላይ የተጠቀሱትን ዋና ክፍሎች አንድ ጊዜ ሳይሆን በየምዕራፉ በተደጋጋሚ የተለያዩ ገፀባህሪያትን በመምዘዝ አስተዋውቆ ግጭት ፈጥሮ ልቀት ላይ አድርሶ ግጭቱን በማርገብ መልሶ ወደ ነበረበት ዋና ታሪክ ወይም ወደ ዋናው ገፀ ባህሪ የብቀላ ጉዞ መግባቱ ላይ ነው። ይህ ደግሞ ሰውየው አንዲት ትንሽ ሴራ ብልጭ ብላላቸው ሳትጠፋባቸው እንደሚፅፉ ምስኪን ፀሃፍት የሴራ አወቃቀር ድሃ እንዳልነበር ያሳያል። የትኛውም ገፀባህሪ ታሪክ ያለምክኒያት ጥራዝ ለማደለብ እንዳልተካተተ ሲገባህ ዱማስ የትልም ቁንጮ መሆኑን ትረዳለህ
ይህን አይነት የሴራ አመሰራረት ለመካን አይነተኛው መንገድ በንባብ እውቀትን ማስፋት ነው።
ተሾመ ዳምጤ ወደ አማርኛ ግሩም አድርጎ መልሶታል። በሆሊውድ መንደር ፊልምም ተሰርቶለታል። ባታዩት እመክራለሁ። "የአለማችን አስቀያሚው የመፅሃፍ ታሪክን ወደ ፊልም ቅየራ" ቢባል ሲያንሰው ነው። በበርካታ የታሪክ ፍሰት ስህተቶች የተሞላ በመሆኑ ፊልሙን ብቻ በማየት መፅሃፉን ካነበቡ እኩል ለውይይት እንዳትጋበዙ . . . .
ያላነበባቹት እድታነቡት የሰኞ ግብዣ ነው
╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ
ፍቅር አሁን !!
140 views09:46