🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የ ኦርቶዶክስ ቅዱሳን አባቶች ትምህታዊ ንግግሮች Wise sayings of holy fathers of orthodox

Logo of telegram channel orthodoxholyfathers — የ ኦርቶዶክስ ቅዱሳን አባቶች ትምህታዊ ንግግሮች Wise sayings of holy fathers of orthodox
Logo of telegram channel orthodoxholyfathers — የ ኦርቶዶክስ ቅዱሳን አባቶች ትምህታዊ ንግግሮች Wise sayings of holy fathers of orthodox
Channel address: @orthodoxholyfathers
Categories: Religion
Language: English
Subscribers: 465
Description from channel

This channel's aim is to help us learn from the spritual life of holy fathers .
ከቅዱሳን አባቶች ትምህታዊ ንግግሮች እንማር ዘንድ የ ተዘጋጀ channel ነው።

ከቅዱሳን አባቶች ትምህታዊ ንግግሮች group https://t.me/joinchat/FXPZVEUP8KLHay0v0d0LuQ
አስተያየት ካላቹ በ @Wiseholyfathers_comment ይላኩልን።

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


The latest Messages

2021-08-23 20:35:18 ​​"በሕይወት የምናሳልፋቸው ሥቃዮች፣በሽታዎች፣ሁከቶች ሕመሞች ወደ አንድ ፍፁም ማንነት እንድንመለስ የሚያመለክቱን ናቸው። ሁላችንም ፍፁም ማንነት ወደምንጋራበት ወደ እግዚአብሔር እንመለስ"

^ሊቁ አውግስጢኖስ^
158 views17:35
Open / Comment
2021-08-11 20:35:57 ​​“መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ።” ምሳ. 31፡29
ክርስቶስን ያከበሩ፤ መንገዱን የተከተሉ ብዙ ሴቶች አሉ፤ እውነትን የመሰከሩ፤ ስለ ቃሉ የኖሩ ብዙ ሴቶች አሉ፤ መስዋዕትነትን የከፈሉ በሰማዕትነት ያለፉ ብዙ ሴቶች አሉ፤ ታላላቅ የምድር ነገስታትን፤ ታላላቅ ነቢያትን የወለዱ ብዙ ሴቶች አሉ፤ ከነዚህ ሁሉ ግን አንቺ ትበልጫለሽ።

ቅድስት ድንግል ሆይ አንቺ እኮ ሰማይ ዙፋኑ ምድር መረገጫው የሆነ፤ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የሰላም አለቃ፤ ሁሉ በእርሱ የሆነ ከሆነውም አንዳችም እንኳን ያለርሱ ያልሆነ፤ ዓለምን ሁሉ ከሞት ወደ ሕይወት የመለሰ፤ መንበሩን የሚሸከሙ ኪሩቤልና ሱራፌል የሚንቀጠቀጡለት፤ የሁሉ ፈጣሪ፤ የሁሉ አምላክ የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ እናት ነሽ። በፊትም አሁንም ወደፊትም ካንቺ በቀር ፈጣሪዋን ልጄ ብላ የምትጠራ ሴት አልነበረችም፣ የለችም፣ አትኖርምም፤ ክርስቶስም እናቴ ብሎ የሚጠራት ብቸኛዋ ሴት አንቺ ነሽ በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ።

እናት ስትሆኝ ድንግል፤ ድንግል ስትሆኝ እናት በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ። ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ብሎ የሚጠራሽ ብቸኛዋ ሴት በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ። እግዚአብሔር መርጦና ጠብቆ ያስቀረሽ ዘር በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ። ለዓለም ሁሉ ድህነት ምልክት የሆንሽ በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ።

እናቴ ሆይ እንግዲህ እኔ ምን ልናገር? ሺህ ቃላትን ብደረድር ያንቺን ክብር ልገልፀውስ እንደምን እችላለው? አዎ አሁንም እላለሁ “መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ።” ምሳ. 31፡29

የቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷ በሁላችን ላይ ይደር፤ ምልጃ ቃል ኪዳኗ ይጠብቀን። አሜን!!!
225 views17:35
Open / Comment
2021-08-07 08:51:23 ​​ሕጻኑም ወጣቱም ወንዱም ሴቱም ዕድሜው የገፋውም ሁሉም በፍቅር የሚጾሟት፡ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ረድዔትና በረከት የሚታፈስባት፡ ፍቅረ እግዚአብሔር በሰው ልቡና የሚሰለጥንባት ፈሪሃ እግዚአብሔር የሚያይልባት፡ የንሰሐና የምህረት ጾም ጾመ ፍልሰታ መጣች፡፡ በዓለም ያሉ ወደ ቤተክርስቲያን በቤተክርስቲያን ያሉ ወደ ገዳማት የሚገሰግሱባት ጾመ ፍልሰታ መጣች፡፡"

እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ
227 views05:51
Open / Comment
2021-07-28 06:43:35 ​​"ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ፀሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው፡፡ እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊቱን በሙሉ ስትፀልይ እደር።"

ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ
232 views03:43
Open / Comment
2021-07-25 23:32:08 ​ቅዱስ ገብርኤል

“የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።” መዝ. 33፡7፡፡ ይህ ጥቅስ የእግዚአብሔር መልአክ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ሰዎች ከእግዚአብሔር ተልኮ በዙሪያቸው ሆኖ ከመከራ እንደሚያድናቸው ያስተምራል፡፡ የመላእክት አንዱ ተግባር መዳንን ይወርሱ ዘንድ ያላቸውን ሰዎች መጠበቅ መሆኑ ተጽፏል፡፡ “ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?” ዕብ. 1፡14፡፡


@wiseholyfathers
አስተያየት ካላቹ በ @Wisecomment_bot ይላኩልን

ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ
237 views20:32
Open / Comment
2021-07-16 06:46:25 ​«አቤቱ በደሌንና ነውሬን የሚያጥብ ዕንባ ሥጠኝ

አቤቱ አንተን የሚያገለግል ዕንባን ሥጠኝ ፣

አቤቱ የሚያቃጥል ዕንባን ሥጠኝ ፤

አቤቱ ከዓይኔ ፈስሶ የአካሌን እድፍ የሚያጥብልኝን ዕንባ ሥጠኝ፡፡

የተጸጸቱ ሰዎችን ዕንባ የምትቀበል ጌታ ሆይ
አንተ የተቀበልከውን ጽኑ ለቅሶ እንዳለቀሰ እንደ ጴጥሮስ ያለ ዕንባን ሥጠኝ

አቤቱ እንደ ባሕር በምትፈስስ ዕንባ እጠበኝ ፤

የማያቋርጥ የዕንባን ጎርፍ አፍስስልኝ

(ውዳሴ አምላክ ዘእሑድ)



@wiseholyfathers
አስተያየት ካላቹ በ @Wisecomment_bot ይላኩልን
275 views03:46
Open / Comment
2021-07-13 06:24:34 ​ወዳጄ ሆይ፦
ቤቱ ቆሽሾ ሳለ ውጫዊ በሩን ብቻ ለማሽቀርቀር ለምን ትጨነቃለህ? ነፍስህ በኀጢአት ተዳድፋ ሳለ ሥጋህን ብቻ ለማስደሰት ለምን ትሮጣለህ? አስቀድመህ ቤቱን (ነፍስህን) ለማስዋብ አትሽቀዳደምምን? አስቀድመህ ለነፍስህ የምታስብ ከኾነ ከሰው እጅ ሳይኾን ከክርስቶስ እጅ ሹመት ሽልማት ትቀበላለህ፡፡ ኹል ጊዜ “የማደርገው ነገር እግዚአብሔር ይከብርበታልን?” ብለህ አስብ እንጂ እንዲሁ በዘልማድ የምትመላለስ አትኹን ብዬ እመክርኻለሁ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲመክረን፡- “እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትኾኑ ወይም ማናቸውም ነገር ብታደርጉ ኹሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት” ያለንም ስለዚሁ ነውና በድርጊቶቻችን ኹሉ እግዚአብሔርን ለማክበር እንዘጋጅ (1ኛ ቆሮ.10፡31)፤ ፡፡

ቅዱስዮሐንስአፈወርቅ
255 views03:24
Open / Comment
2021-06-27 18:27:54 ​​“The Most Holy Mother of God prays for us ceaselessly. She is always visiting us. Whenever we turn to her in our heart, she is there. After the Lord, she is the greatest protection for mankind. How many churches there are in the world that are dedicated to the Most Holy Mother of God! How many healing springs where people are cured of their ailments have sprung up in places where the Most Holy Theotokos appeared and blessed those springs to heal both the sick and the healthy! She is constantly, by our side, and all too often we forget her.”

Book Elder Thaddeus Our Thoughts Determine Our Lives
68 views15:27
Open / Comment
2021-06-26 21:36:20 ​​"God is a Big Heart; He wants your heart to walk with Him- He does not want appearances"

+ Pope Shenouda +
401 views18:36
Open / Comment
2021-06-21 08:27:15 ​​"በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን እርሱም ጌታ ሕይወትን የሚሰጥ ከአብ የሠረፀ ከአብ ከወልድ ጋር በአንድነት እንሰግድለታለን እናመሰግነዋለን እርሱም በነቢያት አድሮ የተናገረ ነው ።"
    ጸሎተ ሐይማኖት
እንኳን ለበዓለ መንፈስ ቅዱስ እና ጾመ-ሐዋርያት አደረሰን አደረሳችሁ።

መልካም ጾም ይሁንልን !!
80 views05:27
Open / Comment