🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

#ሰበር_ዜና ከትናንት በስቲያ ለ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በኒጀርና ማዳጋስካር መካከል በተደ | Asgerami

#ሰበር_ዜና

ከትናንት በስቲያ ለ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በኒጀርና ማዳጋስካር መካከል በተደረገው የማጣሪያ ጨዋታ ሁለቱ ቡድኖች ሳይሸናነፉ አቻ መውጣታቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያ ከምድቡ 2ኛ ሆና ለአፍሪካ ዋንጫ ያለፈችበት ውጤት መሰረዙን BBC focus on Africa ዛሬ ጠዋት ዘገበ።

ለውጤቱ መሰረዝ ምክንያት የሆነው ኒጀርና ማዳጋስካር ከትናንት በስቲያ አድርገውት በነበረው ጨዋታ 3 የኒጀር ተጫዋቾች አደንዛዥ ዕጽ መጠቀመቸው በላቦራቶሪ በመረጋገጡ ምክንያት ነው ተብሏል። ይሄንንም ተከትሎ ኒጀር በአቻ ውጤት ያገኘችው 1 ነጥብ ሙሉ ለሙ ተሰርዞ ለማዳጋስካር የአሸናፊነት ውጤት ማለትም 3 ነጥብ በመሰጠቱ ምክንያት ማዳጋስካር ከምድቡ ከአይቬደሮኮስት ቀጥላ 2ኛ ሆና ለአፍሪካ ዋንጫ ያለፈች በመሆኑ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ዋንጫ ያለፈችበትን እድል አጥታለች ይላል ዘገባው።

ወገኖቼ ተረጋጉ አትደንግጡ ዛሬ ቀኑ አፕሪል ዘፉል ነው እንዳትሸወዱ:: የዛሬዋን ቀን ፈረንጆች April the fool ይሏታል። የማታለል የማሞኘት የመሸወድ ቀን ማለት ነው። ተጠንቀቁ! እንዳትሸወዱ ለማለት ያህል ነው። መልካም ምሽት!