🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የዶሮዎች ነፃ ትግል ፍልሚያ በነ ሼክስፒር ዘመን የእንግሊዛውያን ነገስታት መናሃሪያ የሆነው | Asgerami

የዶሮዎች ነፃ ትግል ፍልሚያ

በነ ሼክስፒር ዘመን የእንግሊዛውያን ነገስታት መናሃሪያ የሆነው ዌስት ሚኒስተር ቋሚ ኮፕ ኪት (የአውራ ዶሮዎች መጋጠሚያ ስታዲየም) ሁሉ ነበረው ። በየሳምንቱ ልክ ዛሬ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ እንደምንለው በሰአቱ የዶሮዎች ፕሪምየር ሊግ ይካሄድ ነበር ። በአሁኑም ጊዜ ልክ እንደ አሜሪካ ቤዝቦል እና ራግቢ በበርካታ አገራት ውስጥ ዝነኛ እና ስመጥር ስፖርት ከሚባሉት ውስጥ አንዱ ኩክ ፋይቲንግ እየሆነ መቷል ።

በአለማችን ላይ በአሁኑ ሰአት የአውራ ዶሮዎች ሊግ በየአመቱ ይካሄዳል ። የአውራ ዶሮ ሊግ ከሚያካሂዱ እና የአውራ ዶሮ ሊግ ውድድርን ለማካሄድ የአውራ ዶሮ ሊግን የሚያስተናግዱ ስቴዲየሞች ካላቸው ሃገራቶች እንግሊዝ ፣ ስፔን ፣ ቬንዙዌላ ፣ ኮሎምቢያ ፣ ኢኮዶር ፣ ሜክሲኮ ፣ ፈረንሳይ ፣ ፓኪስታን ፣ ፊሊፒንስ ፣ ፔሩ እና ፓናማ ናቸው ።

የዶሮዎቹ ፍልሚያ ልክ እንደ እግር ኳሱ ሁሉ የአለም ዋንጫ አለው በታሪክ ድርሳን መዛግብት ውስጥ የተፃፈው የመጀመሪያው ''የአውራ ዶሮዎች'' የአለም ዋንጫ የተካሄደው በ1607 ነው ። በአለም እግር ኳስ ዋንጫ ታሪክ ብራዚል አንደኛ! ጀርመን ሁለተኛ! ጣልያን ሶስተኛ ወዘተ እንደምንለው በአለም የአውራ ዶሮዎች ፍልሚያ ዋንጫ አንደኛ መሆን የቻለችው ሃገር ፓኪስታን ናት ።

ወደ ስቴዲየም ከሚመጡ ታዳሚዎች ውስጥ አብዛኛው የሚመጣው የየራሱን አውሮ ዶሮ ይዞ ነው ። ይህም ለምን ? ምክንያቱም እዛው ስታዲየም ውስጥ የሚፈጠር ክስተት አለ ። እኔ! እኔ! እኔ!እያሉ የራሳቸውን አውራ ዶሮ ወደ መድረኩ በመምጣት እጩ ተወዳዳሪ እንዲሆንላቸው ለውድድር የሚቀርቡበት አንዱ አቋራጭ ስልት ነው ።

ኮክ ፋይት ከዛሬ 6ሺ አመታቶች በፊት ጥንት ፐርሺያ ተብላ በምትጠራዋ በአሁንዋ ኢራን ውስጥ የተጀመረ ጥንታዊ የስፖርት አይነት ነው ። በበፊት ጊዜ ውድድሩ የሚዘጋጀው የንጉሳውያን ቤተሰቦችን በሳምንቱ የእረፍት ቀን ላይ ለማዝናናት ሲባል ነበር ። በዚያን ዘመን ወደ ኮምኪት ገብተው ይህንን አዝናኝ ትርኢት ለማየት የሚፈቀድላቸው የንጉሳውያን ቤተሰቦች እና ከነሱ ቅርበት ያላቸው ብቻ ነበሩ ።

ለነፃ ትግሉ የሚመረጡ አውራ ዶሮዎች የእግራቸው አጥንት እና ስጋ የፈረጠመ እና ክንፋቸውን የመወንጨፍ ሃይል የተባ መሆን አለበት ። እነዚ ተፋላሚ አውራ ዶሮዎች የገበያ ዋጋቸው እስከ 8ሺ የአሜሪካን ዶላር ወይም 320ሺ ብር ይደርሳል።

የአውራ ዶሮዎቹ ባለቤቶች ወደ መወዳደሪያ መድረክ (ኮፕ ኪት) ከመግባታቸው በፊት ይደራደራሉ ወይም የውል ሰነድ ይፈራረማሉ ። ከዚያም ገንዘብ ያሲዛሉ መሸነፍ ማሸነፍ ያለ ነውና ከውድድሩ ቡሃላ ያሸነፈው ዶሮ ለባለቤቱ ገቢ ያስገባል ። የተሸነፈው ዶሮ በሚቀጥለው በቂ ልምምድ አድርጎ ይቀርባል ።

የአውራ ዶሮዎቹ የነፃ ትግል ልክ እንደ እግር ኳስ 90 ደቂቃ ሊቆይ ይችላል ። የመጀመሪያው 45 ደቂቃ እና ሁለተኛ አጋማሽ ተብሎም በሁለት ይከፈላል ። በ90 ደቂቃው ካልተሸናነፉም ተጨማሪ ሰአት ይሰጣል ። አሁንም ካልተሸናነፉ አሸናፊው የሚለየው በእጣ ነው ።

አሸናፊ እና ተሸናፊ የሚለየው
1, ተሸናፊው የመድረክ ቀለበቱን ለቆ ከወጣ
2, ተሸናፊው ፈርጥጦ ከጠፋ
3, አሸናፊው ዶሮ በተሸናፊው ዶሮ ላይ ጉብ ብሎ ማንቁርቱንለ4 ሰከንድ በመንቁሩ ነክሶ ሳይለቅ ከያዘ
4, ተሸናፊው ዶሮ በጣም ከተጎዳ ወይም ከሞተ በማለት ነው።

ለዘመድ እና ለጓደኞቻቹ ሼር አርጉ

@asgerami