🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የ5G ኔትዎርክ በኢትዮጵያ ፦ ኢትዮ ቴሌኮም የ5ኛውን ትውልድ (5G) ኔትወርክን በሃገር ውስጥ ለ | Asgerami

የ5G ኔትዎርክ በኢትዮጵያ ፦

ኢትዮ ቴሌኮም የ5ኛውን ትውልድ (5G) ኔትወርክን በሃገር ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የሙከራ አገልግሎት ለማስጀመር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ካፒታል ጋዜጣ በድረገፁ አስነብቧል።

የሙከራ አገልግሎቱ በመጪው ሳምንት ይጀምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ዘገባው ያስረዳል።

ኩባንያው ፕሮጀክቱን ከቻይናው የሁዋዌ የቴክኖሎጂ ኩባንያ በተገኘ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ነው ተግባራዊ እንደሚያደርግ የተነገረው።

ኢትዮ ቴሌኮም በዝግጅት ላይ ላለፉት ሁለት ወራት ሲሰራ መቆየቱ ተገልጿል።

5G ኔትዎርክ በኢትዮ ቴሌኮም ዋና መ/ቤት እና ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ጨምሮ በአዲስ አበባ በሚገኙ አንዳንድ ቦታዎች የሚተገበር እንደሆነ የካፒታል ዘገባ ያስረዳል።

@tikvahethiopia

@asgerami