🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

'የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት የሚገለጽበት ጊዜ አልተወሰነም።' - አቶ ረዲ ሽፋ ከ12ኛ ክ | Asgerami

"የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት የሚገለጽበት ጊዜ አልተወሰነም።" - አቶ ረዲ ሽፋ

ከ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር የተያያዙ በርካታ ጥያቄዎች ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ደርሰዋል።

የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ረዲ ሽፋ "ፈተናው ገና እየታረመ" መሆኑን ገልጸዋል።

የፈተናው ውጤት የሚገለጽበት ጊዜ አለመወሰኑንም ነግረውናል።

"የፈተናው ውጤት በዚህ ቀን ይገለጻል ተብሎ የተቀመጠ ቀነ ገደብ የለም። ስለዚህ በዚህ ቀን ይፋ ይደረጋል ልንል አንችልም" ብለዋል ዳይሬክተሩ።

የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ለፈተናው ያልተቀመጡ ተማሪዎች ከአንድ ወር በኋላ ፈተናውን እንዲወስዱ ይደረጋል ተብሎ የነበረ ቢሆንም አሁን ባለው ሁኔታ ፈተናውን መስጠት እንደማይቻል ገልጸዋል።

አካባቢዎቹ ገና እየተረጋጉ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ተማሪዎቹ ፈተናውን ለመውሰድ በስነ ልቦና መዘጋጀት እንደሚያስፈልጋቸው ጠቁመዋል።

@tikvahuniversity @TikvahUniversityybot