Get Mystery Box with random crypto!

ተከሳሽ እልህ፣ ቁጭት፣ስሜት በወንጀለኛ ክስ ከልቤ ፍርድ ቤት ለችሎት ቆመዋል ተከሳሽ ፩ እልህ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ተከሳሽ እልህ፣ ቁጭት፣ስሜት

በወንጀለኛ ክስ ከልቤ ፍርድ ቤት ለችሎት ቆመዋል

ተከሳሽ ፩ እልህ

በፍቅር መኖሪያ በተዋደድኩበት
ከሰዉ በመጠበቅ
እልህ ተያይዘህ
ቤቴን አፍርሰሀል
ከማጣት አብረህ ፍቅርን አባረሀል
ወና አድርገሀኛል
ቅጣት ይገባሀል።

ተከሳሽ፪ ስሜት

ከእልህ አብረህ
መታገስ እረስተህ
ትግስትን ንቀሀት
አሻፈረኝ ብለህ
እኔ በሚል ክፋት ስሜትን መርጠሀል
ለቤቴ መፍረሱ እጅህን ሰደሀል
እንዳትከራከር ቅጣት ይገባሀል

ተከሳሽ ፫ ቁጭት

ስሜትና እልህ ባደረሱት በደል
መፀፀት ትክክል
ግን ደሞ በልኩ

ነገር ግን.............

በተጠና ሴራ
ራስን ካለማክበር
ዉስጥን ካለማፍቀር

በመጣ እንቢተኛ አመፀኛ ስሜት
ራስን በመጉዳት

ለ1ኛና 2ት ተከሳሽ አባሪ
ብሎ ፈርዶብሀል የልቤ ስባሪ።

..............................................
ይግባኝ ይፈቀዳል
መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ


በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ

@Tizita_wolde

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19