Get Mystery Box with random crypto!

ፅኑ ቃል ቀኑ ቢተራመስ በጠራራ ፀሃይ ጨረቃ ብትወርስ በውድቅት ለሊት ላይ ፀሀይ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ፅኑ ቃል

ቀኑ ቢተራመስ
በጠራራ ፀሃይ ጨረቃ ብትወርስ

በውድቅት ለሊት ላይ ፀሀይ ብትወጣ
ምሽቱና ቀኑ ሁሉም ቅጡን ቢያጣ
ጊዜው ተገልብጦ ጎልያድ ቢረታ
አልታዘዝ ብሎ ሙሴም ቢያመነታ
መልካም ሚያበጅ ሰው ውርደት ቢከናነብ
አንዱ ላንዱ ተንኮል ቢቀላለብ
ሺህ ዘመን ቢለወጥ
ሺህ ቀኑም ቢቀየጥ
ትላንት ያልኩሽ አለ ዛሬም እንደዚያው ነው
ድሮም እና አሁን ሁሌም 'ወድሻለው


Yoni
Athan @yonatoz

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19