Get Mystery Box with random crypto!

[ ትጉህ ደቀመዝሙር ] አንስታ ስትጥለኝ ዘራፍ ባይ ፎካሪ ድጋሚ ስትጥለኝ ተነሽ ተወርዋሪ ብርጭቆ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

[ ትጉህ ደቀመዝሙር ]

አንስታ ስትጥለኝ ዘራፍ ባይ ፎካሪ
ድጋሚ ስትጥለኝ ተነሽ ተወርዋሪ
ብርጭቆ ነው ብላ ስትጥለኝ ልትሰብረኝ
ከድንጋይ ጠንክሬ ብረት ሁኜ እምገኝ
እግሮቼን ብትቆርጠኝ በደረቴ እምሳብ
አርቄ እማስብ ብልህ እንደ እባብ
ጥገቴን ስትቀማኝ የተስፋ ላም እማልብ
እንጦሮጦስ ጥላኝ አድባር ላይ እምገኝ
በረዶ ነው ብላ እሳት ላይ ስትጥደኝ
ነጥሬ እምወጣ ወርቅ ሁኜ እምገኝ
በእሳት እምትፈትን ህይወት ጨካኝ መምህር
እኔ እጄን እማልሰጥ እጅ መንሳት እንጅ
እጅ መስጠት እማልወድ ብርታቴ እሚጨምር
የህይወት ተማሪ ትጉህ ደቀመዝሙር።

ጥቅምት 19/2014/ዓ/ም

ብርሃኑ ዘላለም