Get Mystery Box with random crypto!

አባቴ ልንገርህ አባቴ የሆዴን አውጥቼ ሳርቅ ካጠገብህ መቼም የሁን መቼ ሁሌም በልቤ ዉስጥ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

አባቴ

ልንገርህ አባቴ የሆዴን አውጥቼ
ሳርቅ ካጠገብህ መቼም የሁን መቼ

ሁሌም በልቤ ዉስጥ ዙፋንህን ይዘህ
ትኖራለህ በልቤ ዉስጥ ለኔ ነግሰህ።

የባትነት ፍቅርክ መቼም ሳይለየኝ
አለ በልቤ ውስጥ ሁሌም ትህ እንዳለኝ

ልጄ ብለህ ስትጠርኝ በጣፋጭ አንደበትህ
ማረገውን ሳጣ ከደስታ ብዛትህ

አያልቅም ተነግሮ አባ የንተ ውለታ
ቢዘከር ቢዘከር ሁሌ ጠዋት ማታ

ብትጨነቅ ለኔ ብትቆጣ ለኔ
ምን ማርግ ....
ችላለው አያሳያኝ የንተን ክፉ ለኔ

የእናት ምትኬ ነህ የአምላኬ ስጦታ
ከሰማይ በታች የለህኝ መከታ

ለኔ ህይወት ስኖር የንተን እረስተህ
በፍቅር ብርሃን ብርሃኔን አብርተህ

በል እረፍ እንግዲ ልርዳህ በተራዬ
ለሁሉም ቀን አለ አሁን ነው ፋንታዬ

ለውለታህ ምላሽ የንሰኝል ቃል
ድንገት ዞር ስትል እንካን ሳቅህ ቁጣህ ይናፍቃል

ክፉ አይንካብኝ እስከ ዘላለሜ
ካንተ በፊት ያርገው ያንተን ክፉ ለኔ

ያላንተ ባዶነው ሳስበው ህይወቴ
ክፉም ሆንክ ጥሩ ኑርልኝ አባትቴ


Lamrot

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19