Get Mystery Box with random crypto!

የገጠሯ ብርሃን የገጠሯ ብርሃን እኔ ነኝ እኔ ነኝ ለእነሱ ያለሁኝ እኔ ሴቷ ጠንክሬ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

የገጠሯ ብርሃን

የገጠሯ ብርሃን እኔ ነኝ
እኔ ነኝ ለእነሱ ያለሁኝ
እኔ ሴቷ ጠንክሬ በገጠር
ሰርቼ በርትቼ ለሀገር
የገጠርን ጭቃ ላደርገው እስፓልት
የገጠርን ኩራዝ
ላደርገውየአምፖልመብራት
የገጠርን ጎጆ ልሰራው አድርጌ ቆርቆሮቤት
ኩሬና ወንዙን ልቀይረው ወደ ንፁህ ውሃነት
ባህልና ወጌን ሳልዘነጋ ሳልረሳው
እቅድ ተስፋ አለኝ እኔው
እቅዴ እንዳይቀር ወድቆ እንዳይሆን መና
ተስፋዬም እንዳይጨልም እሠራለው ገና
እማማ እና አባባ እንዳይቆጡኝ
ሳልል ጫማ ልብስ ሳልል ተራብኩ ተጠማሁኝ
ቢከብድም የገጠሩ ኑሮና ሰራ
የገጠሩ ኑሮና ስራ ከላይ ለሚያየው
ቀላል ነው የሚመስለው
ውስጥ ገብቶ ላየው ግን በጣም ነው
የሚከብደው
ጥዋት ትነሳና ትሰራለች ቁርሱን
እሷ ሳትበላ ታበላለች ቤተሰቧን
ቧንቧ ስለሌለ ወንዝ ነው የምትሄደው
ወንዝም ሄዳ አያልቅ ፈተናው
ሲያስቸግራት ጎረምሳው
ሲያስቸግራት ኮረብታው
ዳገት ቁልቁለቱን
ተራራ አቀበቱን
ስትወጣ በብርታቷ
ስትሄድ በደግነቷ
ውሃውን አግኝታው
ስትመለስ ቀድታው
ሲሰበር ማሰሮው
በጎረምሣው ዱላ
ያ ሁሉ ድካም ይቀራል መና
ቤተሰቦቿም ይቆጧታል ገና
ወዳ አላመጣችው በውበቷ ስትለከፍ
እሷ ጎን ለወንዶች ውበት አትክለፈለፍ
ወንዶቹ በሙሉ ይፈልጓታል እንጂ
ያን ሁሉ ጫና ችላ ተቋቁማው
ሳትል ወዲህ ወዲያ ስትል ወደስራው
እንጀራውን ጋግራው ስትሰራ ወጡን
ከስራዋ እኩል እያስኬደች ትምህርቷን
መብራት የለምና በኩራዝ አጥንታ
ጠዋት ተነስታ ስትሄድ ወደ ት/ቤት
ስራዋን ሠርታ ነው አግዛ እናት አባት
ወንድም የላት እህት እንዳይረዷት
ህልሟን ሳታሳካ እየፈራች እንዳይድሯት
አቋርጣ ብዙ ኪ.ሜ ስትሄድ ት/ቤት
ሰቃይ ነች በትምህርቷም
በስራዋም አታውቅ ወለም ዘለም
ወላጆቿ ልፋትና ድካሟን አይተው
ላኳት ዘመድ ጋ እንድትማር በከተማው
ከተማ ስትሄድ ቢገባትም ግራ ባትለምደው
ስትቆይ ትንሽ ከተማውን ለመደችው
ህልሟንም አሳክታ የአባት የእናቷን ምርቃት አግኝታ
ብርታትም አግኝታ
እንድታየው ነገን ዛሬን በርትታ
ትሠራለች ደክማ ለፍታ
ያቺ የገጠሯ ልጅ ህልሟን ታሳካለች
ነገንም ታየዋለች
ዛሬን ጠንክራ ከሰራች
ለነገ እንጀራዋን ትጋግራለች
ነገን እንድታዩ ዛሬን ጠንክራችሁ ስሩ
የገጠሯ ብርሃን ትላለች እንዳትበሉ ሳትሰሩ
ህልም ካለሽ አላማ ካሰብሽበት እንድትደርሺ
ሁሉንም እያልሽ እሺ
ሲመክሩሽ ጥሩውን እተቀበልሽ
ሲቆጡሽ መጥፎውን እየጣልሽ
ስትወስኚ እያሰብሽ እያሰላሰልሽ
ስታቅጂ የሚጠቅም ለሀገርሽ
ህልምሽን አሳኪ ጠንክረሽ
የገጠሯ ብርሃን አንቺ ስለሆንሽ
ገጣሚ
ሜሮን ሲሳይ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19