Get Mystery Box with random crypto!

ሰባራዉ ልቤ ላይጠገን ዳግሚያ ላይሆን እንደድሮ፣ ሰዉም ላይወጣለት ላይሰምርለት ኑሮ፣ አስመሳዩ በዝ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ሰባራዉ ልቤ
ላይጠገን ዳግሚያ ላይሆን እንደድሮ፣
ሰዉም ላይወጣለት ላይሰምርለት ኑሮ፣
አስመሳዩ በዝቶ ለጉድ ተገፍጥጦ፣
ከፍቅር ገንዘብን ሀብትን አስበልጦ፣
ለሆዱ ላደረ ለጠኔዉ ማርከሻ፣
ፍቅርን በመገፍተር ላሳጣዉ መድረሻ፣
አይራራም አንጀቴ ሆዴን ቅር አይለዉ፣
በመዉደዴ ምትክ ጥቅምን ካስበለጠዉ፣
እንዴትስ ልራራ እንዴትስ አዝናለዉ ፣
ላጎረሰዉ ነካሽ በልቶ ለሚክደዉ፣
የተጎዳዉ ልቤ ትላት ሰዉን አምኖ፣
ስቆ የሸወደዉን ላዩን ተከሽኖ፣
ዳግም ላይሸዉድ ዳግም ላይታለል ፣
ይህ ሰባራ ልቤ ከእንግድህ ወስኖል፣


08/04/2014
ሰይድ አሊ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19