Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያዊ ነን! (በእውቀቱ ስዩም) ፈቅደን ሲመሩን፤ ችቦ ተቀባይ ለሚነዱን ግን ፤ አሻፈረን ባይ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ኢትዮጵያዊ ነን!
(በእውቀቱ ስዩም)

ፈቅደን ሲመሩን፤ ችቦ ተቀባይ
ለሚነዱን ግን ፤ አሻፈረን ባይ
ካልነኩን በቀር፤ ቀድመን ማንዘምት
ከጋሻ በፊት ፤ ጦር የማንሸምት
ኢትዮጵያዊ ነን!
ህብር ያስጌጠው፤ ህይወት ለማብቀል
ዘር ሳናጣራ ፤ የምንዳቀል
ለነዱን ሰይጣን፤ ለመሩን ሰናይ
ጌታን ከገባር፤ ለይተን ምናይ፤
ኢትዮጵያዊ ነን!
ብዙ ህልሞችን፤ ወዳንድ ዐላማ
የሰበሰበ ገርቶ፤ ያስማማ
በደምና ላብ፤ ያቆምነው ካስማ
አገዳ አይደለም፤ የሚቀነጠስ
የዝምድናችን መተሳሰርያ
ሺ ጊዜ ቢከር፤ የማይበጠስ
ኢትዮጵያዊ ነን!
ምን ሆድ ቢብሰን፤ ምን ብንቸገር
እድር አይፈርስም፤ እንኩዋንስ አገር
ብለን በትግስት፤ የምንሻገር
ሲገፈትረን ፤ግፈኛና አጥቂ
ቁልቁል ሲሰደን ፤ሽቅብ መጣቂ
ለውርደት ሲያጩን፤ የምንጀነን
ኢትዮጵያዊ ነን

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19