Get Mystery Box with random crypto!

. አንቺን ሳገኝሽ ነው! ተራ ሰው ነበርኩኝ ልክ አንቺን ሳገኝ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

. አንቺን ሳገኝሽ ነው!


ተራ ሰው ነበርኩኝ
ልክ አንቺን ሳገኝሽ
ከእድለኛ ተርታ ባንዴ ተሰለፍኩኝ

አንቺን ሳገኝሽ ነው
ዘንበል ያለ ጎኔ
የዘመመ አካሌ መስመር የያዘልኝ
አንቺን ሳገኝሽ ነው
ልፍስፍሱ ልቤ
ብኩኑ መንፈሴ በሳቅ የሞቀልኝ
አንቺን ሳገኝሽ ነው
የህይወትን ዳዴ በእርምጃ የጀመርኩት
አንቺን ሳገኝሽ ነው
ህይወት የሚባልን
የሰው ልጅን ማዕድ ልጎርስ የቆረስኩት

አንቺ መግበሽኝ
ህይወትን ቀመስኳት ጣፈጠችኝ በጣም
ለራሴው ማልኩለት
ቅዠት ቢመስል እንኳ ከዚ'ስ ህልም አልወጣም

አንቺን ሳላገኝሽ
ያባከንኩት እድሜ ሊቆጨኝ አሰኘው
ረጋ በል አልኩት
ረፈደ እንጂ አልቀረም እሰየው

ካንቺ ጋራ ያለምኩት
አምሯል ጎዳናየ ሂዱብኝ እያለ
ካይንሽ ያነበብኩት
ሰምሮልኛል መውደድ ናፍቆት እያከለ

መፈቀር ፀጋ ነው ያውም ባንቺ በኩል
....የሆንሽ የፍቅር እኩል

ፍቅር አፈቀረኝ ፍቅርን ወደድኩት
ናፍቆት አበደልኝ ናፍቆትን ናፈቅኩት
ስስት አሳሳሁት ስስቴም አሳሳኝ
ግሩምነት ውጦ ተራነት ተረሳኝ

ይሄ ሁሉ የሆነው
አንቺን ሳገኝሽ ነው!!!

በአቤኒ የተፃፈ


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19