Get Mystery Box with random crypto!

የተወኝ መስዬ የዳንኩ ያገገምኩኝ ከ ረ ም ኩ ኝ። ጠ በ ኩ ኝ። ስመለስ ስቃኘው አልቂያ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

የተወኝ መስዬ
የዳንኩ ያገገምኩኝ
ከ ረ ም ኩ ኝ።
ጠ በ ኩ ኝ።
ስመለስ ስቃኘው
አልቂያለሁ ለካ
ስጋዬ ሲለካ።

ናፍቆት ገዘገዘኝ
መራራቅ ገነዘኝ
ልላወስ አልችልም
ና ስልህ አትችልም።
እስከየት ዝምታ ?
መቼ ትመጣለህ
መቼ ታቅፈኛለህ
የት አገኝሃለሁ
መቼ እጠግብሃለሁ
እንጃ ግን አሞኛል
ስሞሽህ ናፍቆኛል።

መቼ ትመጣለህ?
መች ታክመኛለህ ?!

By dagim hiwot

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19